Addis Zemen (Nov 20, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ማ/ኤ/መ/ባ – ፌብ/1/2019
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን በ2019 በጀት ዓመት በራስ ኃይል ለሚሰራቸው የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች እና የመንገድ ጥገና ሥራዎች አገልግሎት የሚውል የግንባታ ፌሮ ብረት ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
በመሆኑም
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ፈቃድ የአቅራቢነት ምስከር ወረቀት፣ መንግስት መ/ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በታሸገ ኢንቨሎፕ የፋይናንሻል ዋና እና ሁለት ኮፒ የቴክኒካል ፕሮፖዛሉን ዋና እና ሁለት ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ ፣ኮፒ 2 በማለት እና የጨረታማስከበሪያ ዋስትና በተለየ ፖስታ ለብቻው በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ cpo ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ለሁሉም የብረት ዓይነቶች ብር 500,000.00/አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ በማሠራት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖሩባቸዋል:: ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበርያ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው አሽናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈረቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍትነው።
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል።ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ ።
- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም
የስልክ ቁጥር +251113659932
ወልቂጤ– ኢትዮጵያ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን