አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) በግጭትና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችን እና እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን የተለወጡ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) በግጭትና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችን እና እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን የተለወጡ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 21, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

  1. አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) በግጭትና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችን እና  እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን የተለወጡ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
  2. የመኪኖቹን የንብረቶቹን ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች በአንበሳኢንሹራንስ ኩባንያ ጉዳት የደረሰባቸው ተሽከርካሪዎች ማቆያ ቦታ (ቃሊቲ ቆርኪ ፋብሪካ ገባ ብሎ በስተ ግራ በኩል) በስራ ሰዓት ከህዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ማየት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማስገቢያ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 ከቫት በፊት (ሶስት መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ስዓት ጨረታ እስከሚያልቅበት ቀን ድረስ ከዋናው መ/ቤት መግባት ይችላሉ።
  4. ተጫራች መግባት የሚፈልጉትን የእያንዳንዱን ተሽከርካሪ ንብረት ዋጋ በኤንቨሎፕ፣ በራሱ የጨረታ ሰነዱን በማሟላት እስከ ህዳር 25 ቀን 2019 ዓ.ም. እስከ 11:00 ሰዓት ድረስ ዘሪሁን ህንፃ ጎን በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ ቤት ካሣ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ለሚመረቱበት ተሽከርካሪ ንብረት የመነሻ ዋጋ ብር 20% (ሃያ በመቶ) መሆኑን እያሳወቅን መነሻቸው ከ 4,000.00 ብር በታች የሆኑ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1,000.00 (አንድ ሺ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች በማስያዣነት ያስያዙት ገንዘብ ወዲያው ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  6. ጨረታው ህዳር 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ዘሪሁን ህንፃ ጎን በሚገኘው የአንበሳ ኢንሹራንስ በኩባንያው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኘበት ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሸከርካሪ ወይም ንብረት ሙሉ ክፍያ በ5ቀናት ውስጥ መክፈል ይኖርባቸዋል። ክፍያውን ከፈጸሙ በኋላ በ10 ቀናት ንብረቶቹን ካላነሱ ለሃያ ቀናት በየቀኑ ብር 100.00 /መቶ ብር/ የማቆሚያ ቦታ ኪራይ የምናስከፍል ሲሆን በእነዚህ ቀናት ውስጥ ከፍለው ካላነሱ ግን ያስያዙት ገንዘብ በቅጣት መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል።
  8. ለጨረታ ከቀረቡት ተሽከርካሪዎችና ንብረቶች ላይ የሚፈለግ ማንኛውም ዓይነት የስም ማዛወሪያ፤ እና ልዩ ልዩ ወጪዎች ቢኖሩ የጨረታው አሸናፊ ይከፍላል።
  9. ኩባንያው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው።
  11. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
  12. ጨረታውን በተመለከተ ለሚቀርብ ማንኛውም ማመልከቻ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን።
  13. ተጫራቾች ያሸነፉትን ተሽከርካሪ ወደ ስማቸው ለማዞር ከተሸጠበት ቀን ጀምሮ እስከ ሶስት ወር ድረስ ወደ ስማቸው ማዞር ይኖርባቸዋል። ይህ ባይሆን ግን ኩባንያው በተሽከርካሪው ላይ ለሚፈጠረው ማንኛውም ነገር እና ለሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት ኩባንያው ኃላፊነት እንደማይወስድ እናሳውቃለን።
  14. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር  011 635 2283 ወይም 011 618 7000/ 663 2947 በመደወል ወይም በተራ ቁጥር 2 በተጠቀሰው አድራሻ በግንባር ቀርቦ መጠየቅ  ይቻላል

አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *