Addis Zemen (Nov 21, 2026)
የተረፈ ምርት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከታህሳስ 1 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2019 ዓ.ም ለሚያመርተው በየእለቱ ከሚታረዱ ከዳልጋ ከብት የሚገኘውን እርጥብ ቆዳና ከበጎች እና ፍየሎች የሚገኘው እርጥብ ሌጦ፣ የስጋና አጥንት መኖ፣ የዳልጋ ከብት ቀንድ እና ለሳሙና መስሪያ ግብዓት የሚሆነውን የተነጠረ ሞራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራቾች፡–
- በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ ማስረጃ ኮፒ ማያያዝ አለበት።
- የጨረታ ማስከበሪያን በተመለከተ ለዳልጋ ከብት የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሦስት የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) እና በወር ውስጥ ለሚገኝው የበግና ፍየል ሌጦ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) የዳልጋ ከብት ቆዳ ጨረታ ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች የቅድመ ክፍያ ለ10 ቀናት ብር 4,000,000.00 (አራት ሚሊዮን ብር) እና የበግና ፍየል ሌጦ ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች የቅድመ ክፍያ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ለስጋና አጥንት መኖ ለሦስቱ የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) ለዳልጋ ከብት ቀንድ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) እና ለተነጠረ ሞራ ለሦስቱ የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች ለዳልጋ ከብት ቀንድ ምርቱን በሳምንት ውስጥ እንዲሁም ለስጋና አጥንት መኖ ምርቱ በሚመረትበት በሳምንት ሦስት ቀን (ሰኞ፣ማክሰኞ እና ሐሙስ) እና ለተነጠረ ሞራ ምርቱ በተመረተበት ቀን ሙሉ በሙሉ የእጅ በእጅ ሸያጭ በማከናወን ማንሳት የሚችል መሆን አለበት።
- ምርቱን ለመግዛት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች በጨረታ መመሪያ ላይ በተገለፀው መሰረት ይሆናል።
- የዳልጋ ከብት ቀንድ እና የስጋና አጥንት መኖ የጨረታ አሸናፊ ቀደም ተብሎ የተመረተና በመጋዘን ውስጥ ያለውን መግዛት የሚችል መሆን አለበት።
- አሸናፊው የሚኖረው መብትና ግዴታዎች በውል ውስጥ የሚካተት ይሆናል።
- ከቆዳና ሌጦ ውጪ ላሉት ምርቶች የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመከፈል ከድርጅቱ ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይቻላል።
- ጨረታው ለዳልጋ ከብት ቆዳ እና ለበጎች እና ፍየሎች እርጥብ ሌጦ ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም፣ ለተነጠረ ሞራ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም፣ ለስጋና አጥንት መኖ ህዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም እና ለዳልጋ ከብት ቀንድ ህዳር 24 ቀን 2019 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በ 8868 0114163978 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት