የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ለወ/ሮ እመቤት ስዩም አለሙ የተሰጠ ብድር አመላለስ በመያዣነት የተያዙ ንብረቶች (በአርሲ ዞን አሰላ ከተማ ቀበሌ 10/ወልኬሳ ውስጥ የሚገኝ 876 ካ.ሜ ይዞታ፣ ግንባታዎች፣ ዲጂታል የልብስ ስፌት ማሽኖች፣ ጥሬ ዕቃዎች፣ ያለቀላቸው የጨርቅ ውጤቶች እና የቢሮ ዕቃዎች) የ2ኛ ዙር የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Nov 22, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪከት ለወ/ሮ እመቤት ስዩም ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የያዛቸውን ከዚህ በታች በሰንከረዥ የተገለፁትን ንብረቶች በዐዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሻሻለው ዐዋጅ ቁጥር 216/92 እንዲሁም በዐዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሰረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተበዳሪው/የመያዣ ስጪው/ ስም

የሚሸጠው ንብረትና የሚገኝበት ቦታ

የሐራጁ መነሻ ዋጋ

 

የሐራጁ ደረጃ

 

ሐራጅ የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት

ወ/ሮ እመቤት

ስዩም አለሙ

በአሮሚያ ብ/ክ/መንግስት በአርሲ ዞን አሰላ ከተማ ቀበሌ 10 (ወልኬሳ) ውስጥ በ876 ካሜ ይዞታ ላይ ያረፉ ግንባታዎች ድጅታል የልብስ ስፌት ማሽኖች ጥሬ ዕቃዎችና ያለቀለት የጨርቅ ውጤቶች እና የቢሮ ዕቃዎችና ቁሶች

61,041,737.69

 

2ኛ

 

በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ታህሳስ 20ቀን 2019 ዓ.ም ዓ.ም ከ4፡30-6፡30

 

ማሳሰቢያ

1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ለባንኩ በማስያዝ በእለቱ እስከ 4፡30 ሰዓት ድረስ በመመዝገብ መጫረት ይችላሉ።

2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑን በደብዳቤ ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል።

3. ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው በጥሬ ገንዘብ ወይም በከፊል ብድር ሲሆን አሸናፊው በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል።

4. የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው የፕሮጀክቱ ንብረቶች ካሉ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል።

5. አሸናፊው ያስያዘውን ጋብ ከማሚው ዋጋ ሊታሰብለት ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙትን ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመሰሰላቸዋል።

6. የጨረታው አሸናፊ 15 ፐርሰንት የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ከፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወሪያክፍያን ጨምሮ ይከፍላል።

7. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፣ተበዳሪው የተበዳሪ ወኪል እና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ተወካዮች ብቻ ናቸው።

8. ከፕሮጀክቱ ጠቅላላ ይዞታ 1.8 ሜትር ለኮሪደር / ልማት በአሰላ ከተማ መስተዳደር የሚቀነስ መሆኑ እና ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መስሪያ ቤት በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር- 022-211-66-87 ላይ መደወል ይችላሉ።

9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሃራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።  ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሐራጁ አይገደድም።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት