በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሥነ ስርዓት ሳይፈፀምባቸው የተወረሱ እና በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ)፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ አዳዲስ አልባሳት እና የኮንስትራክሽን ማቴሪያል በሐራጅ ጨረታ በኦከሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 25, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ
ሐራጅ ቁጥር 11/2019

በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሥነ ስርዓት ሳይፈፀምባቸው የተወረሱ እና በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ)፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን፣ የተሸከርካሪ መለዋወጫ፣ አዳዲስ አልባሳት እና የኮንስትራክሽን ማቴሪያል በሐራጅ ጨረታ በኦከሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ማሳሰቢያ:- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበረያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et  ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፣ በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች ጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1.ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡

2.በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም ግምታዊ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡

3.የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ ሰነዱን አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች አክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል፡፡

4.ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን፣ የሚያበቀበት፣ እንዲሁም ሰዓት የሚያሳይ ሰንጠረዥ፡-

ተ.ቁ

 

የዕቃው አይነት

 

የጨረታው አይነት

 

በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመበት ቀን

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን

ጨረታው የሚጀመርበት ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት

ስልክ ቁጥር

1

ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ)

 

ሐራጅ

16/03/2019

21/03/2019

4:00

10:00

0221118429/0222118925

2

ኮስሞቲክስ

 

ሐራጅ

16/03/2019

21/03/2019

4:00

10:00

0221118429/0222118925

3

የኮንስትራክሽን ማቴሪያል(Plastic tile spacers)

ሐራጅ

16/03/2019

21/03/2019

4:00

10:00

0221118429/0222118925

4

ኤሌክትሮኒክስ

 

ሐራጅ

16/03/2019

21/03/2019

4:00

10:00

0221118429/0222118925

5

አዳዲስ አልባሳት

 

ሐራጅ

16/03/2019

21/03/2019

4:00

10:00

0221118429/0222118925

6

የተሽከርካሪ መለዋወጫ

 

ሐራጅ

16/03/2019

21/03/2019

4:00

10:00

0221118429/0222118925

7

የቢሮ መገልገያ እቃዎች

 

ሐራጅ

16/03/2019

21/03/2019

4:00

10:00

 

022 111 8429/022 211 8925

5. በጨረታው ሽያጭ የእቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም፡፡

6. በሐራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩ ለጨረታው ዋስትና የሚሆን ማለትም፤ ለምድብ 1 ኤሌክትሮኒክስ 119,100.00፤ ለምድብ 2 ኮስሞቲክስ 406,400.00፤ ለምድብ 3 ኮስሞቲክስ 2,500.00፤ ለምድብ 4 ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) 33,300.00 ብር፤ ለምድብ 5 አዳዲስ አልባሳት 37,300.00 ብር፤ ለምድብ 6 የኮንስትራክሽን ማቴሪያል(Plastic tile spacers) 250,600.00 ብር፤ ለምድብ 7 የቢሮ መገልገያ እቃዎች 1,800.00 ብር፤ ለምድብ 8 የቢሮ መገልገያ እቃዎች 2,300.00 ብር፤ ለምድብ 9 ተሽከርካሪ መለዋወጫ 193,700.00 ብር፤ ለምድብ 10 ተሽከርካሪ መለዋወጫ 768,400 ብር፤ ለምድብ 11 ተሽከርካሪ መለዋወጫ 539,000.00 ብር፤ ለምድብ 12 ተሽከርካሪ መለዋወጫ 1,406,400 ብር፤ ለምድብ 13 ተሽከርካሪ መለዋወጫ 934,000 ብር፤ ለምድብ 14 ተሸከርካሪ መለዋወጫ 781,500.00 ብር፣ ለምድብ 15ተሽከርካሪ መለዋወጫ129,400.00፣ ለምድብ 16ተሽከርካሪመለዋወጫ 186,500.00 ብር፤ እና ለምድብ 21 ተሽከርካሪ መለዋወጫ 26,100.00 ብር በ(Customs Adama Branch) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።

7. በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡትን እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አከባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 የሚገኝ ሲሆን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ማየት እና መጫረት ይቻላል፡፡

8. በሐራጅ ጨረታ እቃዎቹ የመነሻ ዋጋ ያልተወሰነላቸው ስለሆነ የመነሻ ዋጋ በተጫራች የሚሰጥ ይሆናል፡፡

9. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ  የሚታሰብላቸው ሲሆን፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 / ሶስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

10. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

11. ከላይ በተ/ቁ 10 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

12. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም፡፡

13. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

14. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡

NB:- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን መረጃዎች ያላሟሉ ተጫራቾች ቢያሸንፉ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙትን ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ የሚደረግና እቃው በድጋሚ ጨረታ የሚወጣ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

  • የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር  09 05 11 55 11/  011 66 68 828በመደል ማግኘት ይችላሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፡-
  • አዳማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 022 111 8429፤ እና 022 211 8925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት