የመርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ. የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Nov 23, 2026)

ለመጀመሪያ እና ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ.

  • ሎት 1. የሰብል ሽያጭ ለሁለተኛ ጊዜ
  • ሎት 2. ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ለሁለተኛ ጊዜ
  • ሎት 3. የሩዝ መፈልፈያ ማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ ለሁለተኛ ጊዜ
  • ሎት 4. የሰብል ማጓጓዝ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ
  • ሎት 5. የሰብል ማከማቻ መጋዝን ኪራይ የአገልግሎት ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የሚገዛውን መግዛት የሸጠውን መሸጥ እና የሚጓጓዘውን ማጓጓዝ ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መሳተፍ ይችላሉ።

  1.  በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው።
  2.  በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው።
  3.  ጨረታው ከብር 200,000(ሁለት መቶ ሺህ ብር)እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ)ቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለበት፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና ሲፒኦ ሲያስይዝ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል/ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ።
  4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለበት።
  6. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 350 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለሁለተኛ ጊዜ ለወጣው 7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 መግዛት ይችላሉ።
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን ማስያዝ አለባቸው፡፡ ጨረታው 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ለወጣው ለ7 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ7ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።
  8. ቅዳሜ ዩኒየኑ የስራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  9. ጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።
  10. የጨረታ አሽናፊ በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት።
  11. የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን ከአንድ ሎት ውስጥ ለይቶ ወይም ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም፣ አሽናፊ የሚለየው በተናጠል ይሆናል፡፡ አሸናፊው የአሸነፈውን እቃ በፍትህ ውል ከተመረመረ (ከተመዘገበ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል ወይም ይሸፍናል።
  12. አሸናፊው የአሸነፈውን የሚሸጡ ዕቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ሊያነሳ ሲሆን የሚሸጡ ዕቃዎችን የስራተኛም ሆነ ለትራንስፖርት ማንኛውም ወጭ አሸናፊ ይሸፍናል፡፡ ማንኛውም የሚገዙና የሚሽጡ እቃዎች መጠንና ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል።
  13. በሎት 2 ላይ የተጠቀሱት አሮጌ ያገለገሉ ዕቃዎች ውስጥ ከሎት 1ሀ እሰከ ሎት 1 ሐ ድረስ በሶስት ደረጃ የተመደበ ሰለሆነ ከሎት 1ሀ እሰከ ሎት 1ሐ ድረስ የፈልጉትን መርጦ መሙላት ይቻላል፡፡ የሰብል ሽያጭ የሚገኝበት ቦታ ባ/ዳር ከተማ ከዩኒየኑ መጋዝን ሲሆን የሩዝ ሰብል ሽያጭ የሚገኝበት ቦታ ሐሙሲት መጋዝን ሲሆን አሸናፊው መጋዝን ላይ ያለውን ሰብል ለማንሳት ፈቃደኛ የሆነ እና ጥራቱን በአካል በማየት መሙላት የሚቻል ሲሆን ሰብል ሽያጭ የተለያየ አይነት ስለሆነ ሁሉንም ወይም መርጦ መሙልት ይቻላል።
  14. የሰብል ማጓጓዝ ጊዜው እስከ ሐምሌ 30/2019 የሚቆይ ሲሆን ሰብል የመርከብ ሃላፊነት የዬኒየኑ ወይም የመሰረታዊ ህ/ሰ/ማ/የሚወክለው ንብረት ክፍል ሲሆን የማሰጫኛና ማውረጃ ወጭ አሸናፊው ትራንስፖርት አይከፍልም፡፡ የትራንስፖርት ማጓጓዝ ወጪ እና መንገድ ላይ የሚከፈሉ ማንኛውም ክፍያዎች አሸናፊው ትራንስፖርት ይሸፍናል።
  15. የሰበል ማጓጓዝ ትራንሰፓርተር ተጫራች በስማቸው የታደስ የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ፍቃድ ያላቸው መሆን አላባቸው።
  16. የሰብል ማጓጓዝ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ሲፒኦ የሚያዘው ከሁለቱ ውስጥ በአንደኛው ማለትም ከፍተኛ ዋጋ በተሞላው ታሳቢ ሆኖ መያዝ አለበት።
  17. የሰብል ማጓጓዝ ትራንስፖርት የኪሎ ሜትር በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚቀመጥ ሲሆን ከመነሻው እስከ መራገፊያው ድረስ ያለው ኪሎ ሜትር ሲሞላ በትንሹም ቢሆን ሊቀንስና ሊጨምር እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ ቦታውን አውቃችሁ እንድትሞሉ።
  18. የሰብል ማከማቻ መጋዝን ኪራይ ለአምስት ወር የሚቆይ ሆኖ የመያዝ አቅሙ ሰላሳ ሺህ እና በላይ ይሆን ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ የሚራዘም ይሆናል፡ ፡ የመጋዝን ኪራይ አሸናፊ የሚለየው በአንድ ኩንታል ዋጋ ሲሆን ዋጋ የሚሞላው የአንድ ኩንታል ዋጋ ታሳቢ ተደርጎ ይሞላ ምክኒያቱም አሸናፊ የሚለየው ርዝመት፣ ቁመት እና ወርድ 15 በመቶ /1.8*10 መጋዝኑ የመያዝ አቅሙ ዩኒየኑ በሚያዋቅረው ኮሚቴ ተለክቶ በሚገኝው መሰረት ይሆናል፡፡ የምንከራየው የመጋዝን ኪራይ ብዛት ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ ሲሆን አሸናፊውን በቅድም ተከተል የሚያዝ ይሆናል።
  19. ያልተጠቀሱ ሃሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማ የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ።
  20. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  21. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስ/ቁ 09 11 59 05 34/058 320 16 70 መጠየቅ ይቻላል።

የመርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ.