Addis Zemen (Jun 06, 2026)
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሀራጅ ጨረታ ቁጥር 004/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ ተሽከርካሪዎች እና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሀራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡–
በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 004/2018 በ06/10/2018 ዓ.ም ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች ለመጫረት የሚፈልግ ተጫራች ፡–
1. ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የታደሰ መታወቂያ ወይም የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ካርድ ያለው/ያላት
2. ለጨረታ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች ሲሆኑ የሚገኘው ድሬዳዋ ሙዲአነኖ ግቢ የሚገኘው ተሽከርካሪ መጋዘን ውስጥ ነው፡፡
3. የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የሆነ ሰው በጨረታ መሳተፍ አይችልም፡፡
4. በጨረታው ሰነድ ላይ በተገለጸው መስፈርት መሰረት ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ከ29/09/2018 ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ቀኑ 12፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሰነዱን በመግዛት ተሽከርካሪው በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል፡፡
5. ተሽከርካሪውን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
6. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ድሬዳዋ ሙዲአነኖ የሚገኘው ግቢ ውስጥ ነው፡፡
7. ተጫራቾች ለተሽከርካሪው የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ መሆን አለበት፡፡
8. ተጫራቾች ተሽከርካሪውን ለመግዛት ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ 5% በንግድ ባንክ የተረጋገጠ (CPO) በድሬዳዋ ጉምሩከ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
9. የሀራጁ ጨረታ የሚካሄደው በማስታወቂያ መሰረት በእለቱ ጠዋት በ2፡00 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ጨረታው ይጀምራል፡፡
10. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
11. የጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን ተሽከርካሪ አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ተሽከርካሪውን መረከብ ይኖርበታል፡፡
12. ከላይ በተራ ቁጥር 11 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ከፍያውን ፈጽሞ ተሽከርካሪውን ያልተረከበ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፡፡ 13. የጉምሩክ ኮምሽን ድ/ዳ/ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0915460970 (0912885746) መደወል ይቻላል።
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት