Addis Zemen (Jun 28, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር WSSF/SALES/01/2026
የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቁርጥራጭ ብረታብረቶች፣ የተጋቡ እና ያገለገሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
LOT /ምድብ/ |
Description |
|
1 |
ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች |
|
2 |
የተጋባ ጃሪካኖች፣ በርሜሎች፣ |
|
3 |
ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች |
|
4 |
የተለያየ አይነት ያገለገሉ የተሽከርካሪዎች ጎማዎች እና ቸርኪ |
1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ለእያንዳንዱ ምድብ ለየብቻ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጨረታ ተሳታፊው ስም በCBE ACC No 1000473232708 WONJl/ SHOA SUGAR FACTORY ገቢ በማድረግ ከላይ የተጠቀሱት ሽያጮች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ በመግዛት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ። ሜክስኮ ፊሊፕስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 አዲስ አበባ ወይም ወንጂ አቅርቦትና ፋሲሊቲ ማናጅመንት መምሪያ ቢሮ
ለተጨማሪ መረጃ 011 558 5229/022 220 0003/0984 550 101
2. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ለምድብ አንድ 500,000 (አምስት መቶ ሺ ብር)፣ ለምድብ ሁለት 50,000 (ሀምሳ ሺ ብር)፣ ለምድብ ሶስት 50,000 (ሀምሳ ሺ ብር) እና ለምድብ አራት 50,000 (ሀምሳ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በ WONJI/SHOA SUGAR FACTORY ስም ሲፒኦ ወይም ቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት ለጨረታ የተዘጋጁትን እቃዎች ወንጂ በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል በየምድቡ ለየብቻ በማሸግ እስከ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ከመሆኑ በፊት ወንጂ በሚገኘው የአቅርቦትና ፋሲሊቲ ማናጅመንት መምሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
5. ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ወንጂ በሚገኘው የአቅርቦትና ፋሲሊቲ ማናጅመንት መምሪያ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚሆን ሲሆን ትክክለኛው የሥራ ቀን የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሠነዱ ውስጥ ይጠቀሳል ።
6. ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ