ኦርቢስ የንግድ እና ቴክኒክ ማዕከል አ.ማ. በመጋዘን የቆዩ የተለያዩ አይነት የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች እንዲሁም ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ኦርቢስ የንግድ እና ቴክኒክ ማዕከል አ.ማ. በመጋዘን የቆዩ የተለያዩ አይነት የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች እንዲሁም ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Sep 20, 2026)

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና መለዋወጫዎች

የጨረታ ማስታወቂያ

አንጋፋ የአውቶሞቲቭ ኩባንያ ኦርቢስ የንግድ እና ቴክኒክ ማዕከል አ.ማ. በኢትዮጵያ ስመጥር የሆኑትን የመርሰዲስ ቤንዝ እና ሬኖልት ተሸከርካሪዎች ብቸኛ አስመጪ መሆኑ ይታወቃል።

በመሆኑም ኩባንያችን በመጋዘናችን የቆዩ የተለያዩ አይነት የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን (የመርሰዲስ የቦሽ፣የሬኖልት፣ቦማግ) እና የኮሚኒዩኬሽን መሳሪያዎችና መለዋወጫዎች (የሞቶሮላ) እንዲሁም መርሰዲስ ቤንዝ፣ ሬኖልት ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሽጥ ስለሚፈልግ ህጋዊ ተጫራች የሆናችሁ ሜክሲኮ በሚገኘው /ቤታችን ዘወትር በሥራ ሰዓት በመገኘት የመኪኖቹን እና የመለዋወጫዎቹን ዓይነት እና ዝርዝር ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1.ተጫራቾች ንብረቶቹን ከመስከረም 11 ቀን 2019 . እስከ መስከረም 22 ቀን 2019.ም ከጠዋቱ 0200-1030 ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ዝቅ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል ተገኝተው መመልከት ይችላሉ።

2.ጨረታው አርብ መስከረም 22 ቀን 2019.ም ከቀኑ 1030 ተዘግቶ በማግስቱ መስከረም 23 ቀን 2019. ከጠዋት 04:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

3.ለጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይቻላል።

4.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሲ.. ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።

5.በጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ

6.ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

7.ለበለጠ መረጃ መለዋወጫዎችን በተመለከተ፡

በስልክ ቁጥር፦ 0913773127 እንዲሁም ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ በስልክ ቁጥር 0974656420 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

ኦርቢስ ንግድና ቴክኒክ ማዕከል አ.ማ

ስልክ፡ 115516211/115510078


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *