የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተለያዩ እቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተለያዩ እቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


2merkato.com (Nov 13, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 6/2019

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤

  1. ድርጅቱ መብራት፣ ውሃ፣ የአዳራሽ ኪራይ እና የክበብ ዕቃዎች በነፃ አቅርቦ የክበብ አገልግሎት ግዥ ማግኘት ይፈልጋል
  2. የብር መቁጠሪያ ማሽን፣ የውሃ ማጣሪያ፣ የተለያየ መጠን ያላቸው ፍሪጆች፣ አውቶክሌቭ ማሽን/ለክሊኒክ/ ግዥ፣
  3. የተለያየ መጠን ያላቸው ማኑዋል እና ዲጂታል ሚዛኖች፣ ግራይንዲንግ ማሽኖች፣ የማዳበሪያ መስፊያ ማሽን፣ የማሸጊያ ማሽኖች ግዥ፣
  4. የተለያዩ ኬሚካሎች ግዥ፣
  5. ለህንፃ እና ለቢሮ ዕቃዎች ጥገና የሚያገለግሉ ዕቃዎች ግዥ፣
  6. የተሽከርካሪ መለዋወጫ ግዥ፣
  7. Automatic Water Softener Machine Maintenance፣ እና የማቀዝቀዣ ማሽን ጥገና ግዥ፣
  8. የተለያዩ የእስፖርት ትጥቆች ግዥ፣
  9. ጋልቫናይዝድ ፐርፎሬትድ ሺት ሜታል እና ሌሎች ዕቃዎች ግዥ፣
  10. የተለያዩ ቶነሮች እና የቴክኖሎጂ ዕቃዎች ግዥ፣
  11. የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፡- በኤሌትሪክ የሚሰራ እስከ 30 ሰው የመጫን አቅም ያለው ተሽከርካሪ፣ 1/አንድ/ ቶን ክብደት የመጫን አቅም ያለው የኤሌክትሪክ ሻንሲ ካቢን ግዥ፣ 3/ሦሥት/ ቶን ክብደት የመጫን አቅም ያለው የኤሌትሪክ ሻንሲ ካቢን ግዥ፣ በኤሌክትሪክ የሚሰራ አውቶሞቢል፣ በኤሌትሪክ የሚሰራ ፎርክሊፍት፣ የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጀር ግዥ፣
  12. የተለያዩ መሳሪያዎች ግዥ፡- የበሬ ክብደት ማንሻ ማሽን፣ የፍርንባ መቁረጫ ማሽን፣ የጐድን መሰንጠቂያ ማሽን፣ የሸሆና ጥፍር
    መንቀያ ማሽን፣ ሰርቦ ሞተር፣ Electrical Motor with Gear BoX ግዥ፣
  13. የተለያዩ ፓምፖች ግዥ፡- የሞራ መሳቢያ ፓምኘ፣ ሰብመርሰብል ፓምኘ፣ Submersible trash pump፣ ላሚል ፓምኘ ግዥ፣

ማንኛውም ተጫራች፡-

  • በዘርፉ ወይም በተመሳሳይ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር(TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ክሊራንስ እንዲሁም በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  • ከተራ ቁጥር 1-10 ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ እንዲሁም ከተራ ቁጥር 11-13 ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 1000/አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል በስራ ሰዓት ከግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3ዐ ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ማግኘት ይችላል፣
  • የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድቦንድ/ ለሚጫረትበት የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
  • የጨረታ ሰነዶችና ከጨረታው ጋር ተያያዥ የሆኑ ሠነዶችን በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
  • ጨረታው ህዳር 24 ቀን 2019ዓ.ም የሚከፈት ሲሆን ከተራ ቁጥር 1-7 የተዘረዘሩት እቃዎች ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡3ዐ ሰዓት እንዲሁም ከተራ ቁጥር 8-13 የተዘረዘሩት እቃዎች ከቀኑ 8፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡3ዐ ሰዓት የጨረታ ኮሚቴዎች፣ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል፡፡በጨረታ አከፋፈት ሂደት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉለውም፡፡
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ዐ11466-47-05 መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት