Your cart is currently empty!
የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ የተለያዩ እቃዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር APF/08/2018/Local
የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ የሚገኝ ሲሆን ፋብሪካው
- ሎት 1 Water cooled Chiller machine with compatible cooling tower ብዛት set 01
- ሎት 2 የፎርክ ሊፍት እና የኮስትር ተሽከርካሪዎች ጎማ ብዛት በቁጥር 27
- ሎት 3 የተለያዩ የቤተ ሙከራ ማሽኖች መካኒካል እና ኤሌክትሪካል መለዋወጫዎች (ብዛትና ዓይነታቸው በጨረታ ሠነዱ ላይ የሚገለፅ)
- ሎት 4 የተለያዩ የማሽን መካኒካል እና ኤሌክትሪካል መለዋወጫዎች (ብዛትና ዓይነታቸው በጨረታ ሠነዱ ላይ የሚገለፅ)
- ሎት 5 Yellow Master Batch ብዛት 575kg እና
- ሎት 6 Black Master Batch ብዛት 32,500kg
- ሎት 7 Different Green House Sheet Baw Materials/Additives (ብዛትና ዓይነታቸው በጨረታ ሠነዱ ላይ የሚገለፅ)
በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾች፡-
1. ለ2017/18 በጀት ዓመት የታደሰ የሕጋዊነት ማረጋገጫ ሠነዶችን ማቅረብ አለበት።
2. ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በፋብሪካው የፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 108 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
3. ወይም በአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ስም በኢትዮጵያን ንግድ ባንከ ባህርዳር ቅርንጫፍ በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013149996 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኙን በኢ-ሜይል አድራሻችን {HYPERLINK ” mailto:amharapipefactory@gmail.com” በመላክ የጨረታ ሠነዱን ሶፍት ኮፒ በኢ-ሜይል በማግኘት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
4. ተወዳዳሪ ድርጅቶች ለተወዳደረበት ዕቃ ያቀረበውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በፋብሪካው ስም በማሰራት የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው። የባንክ ዋስትና ውበባንኩ ባ/ዳር ቅርንጫፍ በኩል ስለትክከለኛነቱ ማረጋገጫ የተሰጠበት መሆን አለበት።
5. የሕጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ፎቶ ኮፒ እና የዕቃዎችን ዝርዝር የቴክኒክ መስፈርት በአንድ ላይ Temical Bad Ofer) በማለት ለብቻው ከዋጋ ማቅረቢያው (Financial Bid Offer) በመለየት በፖስታ በማሸግ (ዋና ወይም ቅጂ ብሎ በጽሑፍ በመለየት) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. እንዲሁም ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን (Financial Bid Offer) እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን ለብቻው ከቴክኒክ መስፈርት በመለየት በፖስታ በማሸግ (ዋና ወይም ቅጂ ብሎ በጽሑፍ በመለየት) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ15ኛው ቀን ቢሮ ቁጥር 206 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 ይከፈታል። 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ከሆነ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
8. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 206 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 35 98 37 29/ 09 18 70 18 26 መደወል ይችላሉ።
አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ
ባህርዳር