Your cart is currently empty!
ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት የቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ ስክራፕ የተደረጉ ተሽከርካሪዎች፤ ማሽነሪዎች እና አገልግሎት ሰጥተው ወደ መጋዘን የተመለሱ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በኪሎ ግራም ዋጋ ለብረታ ብረት አቅላጭ በውድድር እንዲሸጥ በፈቀደው መሰረት አገልግሎት ሰጥተው ወደ መጋዘን የተመለሱ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን እና የመሳሰሉትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
አገልግሎት ሰጥተው የተመለሱ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች የግልፅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DIS 02/2017
ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በቁጥር ገ/ኢ/1/53/168 ከገንዘብ ሚኒስቴር ለድርጅታችን በቀጥታ በፃፈው ደብዳቤ በየተቋማቱ የሚገኙ የቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ ስክራፕ የተደረጉ ተሽከርካሪዎች፤ ማሽነሪዎች እና አገልግሎት ሰጥተው ወደ መጋዘን የተመለሱ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በኪሎ ግራም ዋጋ ለብረታ ብረት አቅላጭ በውድድር እንዲሸጥ በፈቀደው መሰረት አገልግሎት ሰጥተው ወደ መጋዘን የተመለሱ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን እና የመሳሰሉትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የገንዘብ ሚኒስቴር ለብረት አቅላጭ በኪሎ ግራም የገቢያ መነሻ ዋጋ ብሎ በወሰነው መሰረት በብረታ ብረት አቅላጭነት የተሰማሩትን በገበያ በማወዳደር ለመሸጥ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል። ይሁን እንጂ አገልግለው የተመለሱ የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች በወጣው ጨረታ ገዥ ባለመቅረቡ በድጋሚ ባሉበት ሁኔታ ለመግዛት ፍላጎት ላለው ማንኛውም ተጫራች መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆነ ድርጅት/ግለሰብ በድርጅታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቅዳሜ ነሐሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በኋላ ባሉት የሥራ ቀናት ማለትም ከሰኞ ነሐሴ 19 ቀን 2017ዓ.ም ጀምሮ እስከ አርብ ነሐሴ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ በመክፈል ለገሃር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ስድስተኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት መምሪያ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
ጨረታው ሰኞ ነሐሴ 26 ቀን 2017ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልፅ የሚከፈት ሲሆን ሰነድ የገዙ ተጫራቾች በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 6ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነዱን በፖስታ ውስጥ በማሸግ እስከ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ተቋሙ ጨረታውን ከመከፈት አይታገድም።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስለ ጨረታው የበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 554 9257/ 09 51 41 42 04 ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል።
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ