Your cart is currently empty!
የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በ2018 በጀት የተለያዩ የሽያጭና የአገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001 ሽያጭና አገልግሎት/18 ዓ.ም
የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በ2018 በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የሽያጭና የአገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለመሸጥ ይፈልጋል፡–
1ኛ ለምግብነት የሚውል ንፁህ ስንዴ፣ ጤፍ፣ ገብስ፣ ቦሎቄ እና የእህል ሰብል ብጣሪዎች ሽያጭ
2ኛ የ2017/2018 ዓ/ም የሂሳብ ኦዲት አገልግሎት ጨረታ
3ኛ የትራንስፖርት ማጓጓዣ አገልግሎት ጨረታ
4ኛ ያገለገለ መኪና፣ የእርሻ ትራክተር ከነማረሻው የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ
በዚሁ መሠረት፡
- ተጫራቾች በሥራ ዘርፉና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች ህጋዊ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና የዘመኑን የመንግሥት ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ውድድር ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) በጨረታ ሰነድ ላይ የሚገለጽ ይሆናል።
- የጨረታው ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 400.00 በመክፈል በሀዋሳ ከተማ በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ፖስታ/ኤንቨሎፕ/ በማድረግ ኦሪጂናልና ኮፒውን ለየብቻው ከተጓዳኝ ማስረጃዎች ጋር በማደራጀት በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ን/አስ/ ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ15ኛው ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በወጣ በ15 ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጐ በእለቱ በ8፡30 ሰዓት በድርጅቱ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ተጫራቾች / ህጋዊ ወኪሎቻቸው/በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይከፈታል።
- ድርጅቱ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች በሚዘጋጀው የጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።
በስልክ ቁጥር 046 220 1752/2285/2117
የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት
Accounting System Design cttx, cttx Accounting and Auditing, cttx Agriculture and Farming cttx, cttx Disposal Sale cttx, cttx Food and Beverage cttx, cttx Food Items and Drinks cttx, cttx Freight Transport cttx, cttx Machinery and Equipment cttx, cttx Other Sales cttx, cttx Products and Services cttx, cttx Raw Materials and Supplies cttx, cttx Rent cttx, cttx Sales, cttx Transportation Service cttx, cttx Vehicle and Machinery Foreclosure cttx, cttx Vehicle and Machinery Sale cttx, cttx Vehicle cttx, cttx Warehousing, Disposals and Foreclosure cttx, Transit and Transport Service cttx