Your cart is currently empty!
በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜ ውርስ የተደረጉ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ጫማ፣ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ የወጥ ቤት እቃ እና ጃንጥላ በግልፅ እንዲሁም ሞረድ፣ charge pin፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ usb cable፣ bearing and radiator፣ belt፣ የወጥ ቤት እቃ መዳብ እና የውሀ ቆጣሪ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 26, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር -08/2018 ዓ.ም
በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜ ውርስ የተደረጉ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ፣ጫማ፣ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ኮስሞቲክስ፣የወጥ ቤት እቃ እና ጃንጥላ በግልፅ እንዲሁም ሞረድ፣charg pin፣ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ usb cable፣ bearing and radiator፣ belt የወጥ ቤት እቃ መዳብ እና የውሀ ቆጣሪ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተጫራቾች መመሪያ የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹ፡-
1, በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ግለሰብ መጫረት ይችላል።
2. የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛዉንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ማቅረብ አያስፈልገዉም።
3. በተጠቀሰው መስፈርት በጨረታ የሚሸጠው እቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፤ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው (6) ቀን 03፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታው የዕቃዎችን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው ስምም ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው እና በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፁትን በኤንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 3፡50ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
6, የጨረታ ማስታወቂያዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ፅ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልፅ ጨረታዉ 3፡50 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሀራጅ ጨረታዉ 4፡30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል።
7. ተጫራቾች በጨረታዉ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ 05 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል። በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለመ/ ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃዉ እንደገና ለጨረታ ይቀርባል።
8.ተጫራቾች ለእቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሸናፊ ከሆኑ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል።
9. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ እቃዎችን በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እና ስድስተኛው ቀን ጧት 3፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ።
10, ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ እቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሀራጅ ጨረታ እቃዎች አንድ መቶ ሺህ ብር (100,000) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
11. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 033 551 06 93 ደውለዉ መጠየቅ ይችላሉ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት