በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካዎች ያገለገሉ የተለያየ ሳይዝ ያላቸው የቀላል ተሽከርካሪ እና የከባድ ማሽነሪ ጎማዎች፤ የፕላሲቲክ ቦቲ ጫማዎችን እና ቁርጥራጭ ብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 27, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

አንደኛ ዙር ብሔራዊ ልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አሽጨ/001/ኦኩስፋ /1 እና 3/2018

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካዎች ያገለገሉ የተለያየ ሳይዝ ያላቸው

  • የቀላል ተሽከርካሪ እና የከባድ ማሽነሪ ጎማዎች
  • የፕላሲቲክ ቦቲ ጫማዎችን እና
  • ቁርጥራጭ ብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

  1. ማንኛውም ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም ህጋዊ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ሰነድ/መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶች የሚገኙበት አድራሻ፡ክልል በምዕራብ ኢትዮጵያ ቤንች ማጂ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ እና ክልል ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ወረዳ ሳላማጎ ወረዳ ኦሞ  ኩራዝ ቁጥር-1 ስኳር ፋብሪካ ግቢ ነው።
  3. ጨረታው ጥቅምት 28 ቀን /2018 . ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ(ፖስታ) በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን 28/02/18 ዓም ከቀኑ 830 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
  4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በሃርድ ኮፒ እና 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በሶፍት ኮፒ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት 230-6፡00 ከሰዓት በኋላ 730 – 1030 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት 230-600) ከታች በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  5. ለሽያጭ የቀረቡ እቃዎች ወይም ንብረቶችን ዝርዝር የያዘው መደበኛ የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት፤ የመወዳደሪያው ሰነድ የሚገባበት እና ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ፡ኦሞ ኩራዝ ቁጥር -1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል በሚያስገባው አስፓልት ከጦር ሃይሎች ወደ ዘነበ ወርቅ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ 3 ቁጥር ማዞሪያ / ቶታል ገባ ብሎ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ላይ ስልክ ቁጥር 09-10-12-06 28 እና 09-13-54-47-31 አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ፤
  6. በተጨማሪ የጨረታ ሰነድ ለመሸጥ ብቻ የሚያገለግል የሻጭ አድራሻ ኦሞ ኩራዝ ስኳር ብሪካ ቁጥር-1 እና 3 ስልክ ቁጥር 09-16-17 08 34 ኩራዝ፤
  7. ለሽያጭ የቀረቡ ዕቃዎች ርክክብ የሚፈፀመው ቦታ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር1 እና 3 ስኳር ብሪካ ግቢ ውስጥ ነው።
  8. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ብቁ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ጥቅል ዕቃዎች ቀጥሎ የተመለከተውን የብር መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡
  • ጥቅል (ሎት-1) የተሽከርካሪ የጎማ ሽያጭ ብር 75,000.00 (ሰባ አምስት ሺህ ብር)
  • ጥቅል-1 (ሎት-2) የፕላስቲክ ቦቲ ጫማ ሽያጭ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)
  • ጥቅል‐1 (ሎት-3) ቁርጥራጭ ብረቶች ሽያጭ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)

10. ለሽያጭ የቀረቡ ዕቃዎች ርክክብ የሚፈፀመው ቦታ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር-1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ግቢ ውስጥ ነው።

11. ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 60(ስልሳ) ቀናት ነው፡፡

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ