Your cart is currently empty!
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በዋናው መ/ቤት እና በሥሩ በሚያስተዳድራቸው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሲገለገልባቸው የቆዩ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ ጎማና ባትሪ፣ የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች፣ የቢሮ መገልገያ፣ የቢሮ ፈርኒቸር፣ የግንባታና የፓርቴሽን ዕቃዎች እና ሌሎች ባሉበት ቦታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 06, 2026)
ያገለገሉ ንብረቶች ጨረታ ማስታወቂያ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢፓልኮ/ንማግጨ/01/2018
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በዋናው መ/ቤት እና በሥሩ በሚያስተዳድራቸው ቅርንጫፍ ጽ/ ቤቱ ሲገለገልባቸው የቆዩ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ የተሸከርካሪ ጎማና ባትሪ፣ የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች፣ የቢሮ መገልገያ፣ የቢሮ ፈርኒቸር፣ የግንባታና የፓርቴሽን ዕቃዎች እና ሌሎች ባሉበት ቦታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች ግለሰቦች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
1. በማንኛውም ዘርፍ ህጋዊ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው ድርጅት ወይም ማንኛውም ግለሰብ።
2. የጨረታውን ሰነድ ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ተ.እ.ታ አካቶ በመክፈል ኮዬ ፈጬ፣ ከኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ፊት ለፊት ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የአንድ ማዕከል አገልግሎት ህንጻ ግራውንድ ፍሎር (የንብረት አስተዳደርና ጠ/አገልግሎት መምሪያ) በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎች መመልከት ከፈለጉ ከጨረታው መክፈቻ ዕለት አስቀድሞ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት (ዋናው መ/ቤት፣ ቂሊንጦ ኢ ፓርክ፣ ips/ሃያ ሁለት አካባቢ፣ አዲስ ኢንዱስትሪ መንደር ሣሪስ ካዲስኮ (ትራንስ ኢትዮጵያ ፎቅ ላይ ) በሚገኙ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት እና በቅርንጫፍ ጽ/ቤት/ፓርኮች መጋዘን በአካል ተገኝተው መመልከት ይችላሉ።
4. ጨረታው የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ላይ በኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
5. የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ በታሸገ ፖስታ (Envelope) በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት የጠቅላውን የጨረታ ዋጋ 20% “በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን” ስም የተዘጋጀ ሲ.ፒ.ኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ከኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
7. አሸናፊ ድርጅት የአሸናፊነት ደብዳቤ በተሰጠው በ 10 ቀናት ውስጥ የንብረቱን ጠቅላላ ዋጋ በመክፈል ንብረቱን ማንሳት ይጠበቅበታል።
8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 011 658 2885
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን