Your cart is currently empty!
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን አገልግሎት ለሚሰጣቸው መ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን የተለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 11, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 002/2018
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን አገልግሎት ለሚሰጣቸው መ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን በ7/ ሰባት/ሎት ማለትም፡–
- ሎት 1 –የቦቴ ውሃ አቅርቦት
- ሎት 2- የመጸዳጃ ቤት አገልግሎት፣
- ሎት 3 – መጋረጃዎች ፣ የወለል ምንጣፍ እና የአዳራሽ የወንበር ልብስ፣
- ሎት 4- የተለያዩ የዲኮር እና የድንኳን ኪራይ አገልግሎት
- ሎት 5- የስጦታ ዕቃዎች፣
- ሎት -6- የተለያዩ የጽዳት እቃዎች
- ሎት 7- የመኪና ጌጣጌጥ እና
- ሎት 8- ለህፃናት ማቆያ/ዲኬር/ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎች ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት አሟልቶ በጨረታው መወዳደር ይችላል።
1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣ ንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው ፣ ግብር ከፋይነት ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አቅራቢነት ማስረጃ ያለው፣ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆነ፣
2. በዘርፉ በገንዘብ ሚኒስቴር በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም በ2018 በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ አካል በጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ የሚሰጥ የታደሰ የምስከር ወረቀት /ክሊራንስ/ ማቅረብ የሚችሉ
3. የጨረታ ማስከበሪያ፡– ለእያንዳንዱ ሎት ከአጠቃላይ ለበጀት ዓመቱ ከተበጀተው በጀት ከ0.5- 2% የተሰላነው
|
ሎት 1 |
ሎት 2 |
ሎት 3 |
ሎት 4 |
ሎት 5 |
ሎት 6 |
ሎት 7 |
ሎት 8 |
|
23,900.00 |
10,000 |
10,000 |
5,000 |
5,000 |
3,000 |
5,000 |
8,000 |
4. በእያንዳንድ ሎት ለብቻው በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ADDIS KETEMASUB_CITY ADMINSTRATOIN PUBLIC SERVICE & HUMAN RESOURECE DEVELOPMENT OFFICE PURCHASING ADMINISTRATION SUPPORTIVE PROCESS በሚል ስም የተሰራ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
5 የድጋፍ ደብዳቤ ለጨረታ ማስከበሪያ የተፃፈ ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ብቻ ነው ሰነድ በነፃ እንዲወስዱ ተብሎ ከተፃፈ ለሰነድ መወስጃ ብቻ ነው የሚያገልገለው
6 የድጋፍ ደብዳቤ ካደራጀው አካል የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ይዞ ሲመጡ በነፃ ይወስዳሉ አምራቾች/ በጥቃቅንና አነስተኛ በተደራጁ ማህበራት/ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ በሚያመርቱት ምርት ላይ 3% አስተያየት ይደረግላቸዋል።
7 የሚታዘዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ተቀባይነት የሚኖረው የሲፒኦ ቁጥር የሚታይ ከሆነ፣ የተጫራቹን ስም በግልፅ የሚነበብ ከሆነ ሲፒኦ ጀርባ ላይ የባንኩ ማረጋገጫ ማህተም ያለው ከሆነ ብቻ ነው
8 ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10/አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 በአ/ከ/ክ/ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የፋይናንስ ቡድን 6ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 መውሰድ ይችላሉ።
9 በክፍል 6 ባዶ በቴክኒክ መመዘኛዎች ላይ ተሟልቶ፣ ተፈርሞ እና ማህተም ተደርጎ፣ በሁሉም ገጽ ላይ ተፈርሞ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎ ሙሉ የጨረታ ሰነድ /መመሪያ/ ተመላሽ ይደረጋል
10 የጨረታ ሰነዱ ቴክኒካል ዋናውን አንድ/1/ እና ፎቶ ኮፒ /1/ ፋይናንሺያል ሰነድ ዋናውን አንድ/1/ እና ፎቶ ኮፒ አንድ/1/ ለየብቻ በፖስታ ታሽጎ በድምሩ አራት/4/ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ኦርጅናል/ኮፒ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል በሚል በፖስታው ላይ በመግለጽ /በመፃፍ/ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን አ/ከ/ከ/ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን 6ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ማስገባት ይኖርበታል።
11 የጨረታ ሰነድ ለመግዛት እና ፖስታውን ለማስገባት ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ማስገባት ይችላሉ። በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋቱ 3፡00 የጨረታው ሳጥን የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ ቀን ጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፤ ነገር ግን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
12 መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡– 011-8-27-99-79 / 011-8-95-92-23 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፤
አድራሻ፡– አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከግሩም ሆስፒታል ከፍ ብሎ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የፋይናንስ ቡድን፤ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን