የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተዉና ተወርሰው የሚገኙ ዕቃዎች በግልፅና በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተዉና ተወርሰው የሚገኙ ዕቃዎች በግልፅና በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (May 09, 2026)

የተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 34/2018

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን //ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተዉና ተወርሰው የሚገኙ መገናኛ መሣሪያዎች አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች የቤትና ቢሮ መገልገያ ዕቃዎች የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች እና የሞተር ሣይክል መለዋወጫዎች፣ ያገለገለ ሞተር ሳይክሎች እና ያገለገለ ተሽካርከሪ በግልፅና በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

1. የግልፅ ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ /ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡ ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነውን ማንኛዉንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡

2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 200 እስከ 600 ከሰዓት 700 እስከ 1100 ሰዓት ቅዳሜ 200 እስከ-600 ሰዓት ድረስ ብቻ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) በማስገባት በስልክ ደውለው በማሳወቅና ስሊፕ በመላክ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይቻላል፡፡

3. ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ለጨረታውማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪ ለሃራጅ ጨረታ ለሚሳተፋ ተጫራቾች ለኮድ 01 ለመዋቢያና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች እና ኮድ 07 ያገለገለ ተሽካርከሪ ለእያንዳንዱ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ለኮድ 02 0304 05 እና ኮድ 06 ብር 30,000 (ሠላሳ ሺህ ብር (CPO) ለእያንዳንዱ ኮድ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የንብረቶቹን ናሙና በመደበኛ የስራ ሰዓት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 6ኛው (ስድስተኛው) ቀን የግልፅ ጨረታው ጠዋት 400 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 405 ሰዓት ፔፕሲ ፋብሪካ ፊትለፊት በሚገኘው ሃዋሳ //ቤት አዲሱ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ተከፍቶ ሂደቱ ካለቀ ከ10 ደቂቃ በኋላ የሐራጅ ጨረታው የሚጀምር ይሆናል። ነገር ግን የጨረታው ቀን እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ይካሄዳል።

5. ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ ከነቫት በሚለው መስመር በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ወይም ፖስታ መቅረብ አለባቸው። ከዚህ ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ለመቀበል አይገደድም።

6. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችልም በተጨማሪ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥ እና ማሻሻል አይችልም፡፡

7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም፡፡

9. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በእለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል፡፡

10. ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ የሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በተጨማሪ ጽ/ቤቱ የማይነበብ የሰነድ ኮፒ የመቀበል ግዴታ የለበትም፡፡

11. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ በጨረታ ላይ ይወጣል፡፡

12. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡- 046-212-53-96/046-212-65-95

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት