በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት በደቡብ ኦሞ ዞን የሣላማጎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ፑል ማዕከል የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች በሐራጅ ግልጽ ጨረታ ሽያጭ ዘዴ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 19, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር//-01/2018

በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት በደቡብ ኦሞ ዞን የሣላማጎ ወረዳ ፋይናንስ /ቤት በወረዳው ፑል ማዕከል ያገለገሉ ቀላልና ከባድ መኪናዎች፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የመኪና ባትሪዎች፣ ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች፣ ብስከሌቶች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች(ፍርጆች)፣ ትላልቅ ጄነርተሮች፣ መካከለኛ የመስኖ የዉሃ ፓምፕ ጄኔርተሮች፣ የሕከምና መገልገያ ቁሳቁሶች፣ ወፍጮዎች፣ የክረቼር ዲናሞ የፋብርካ ውጤት ዕቃዎች ከስርዓተ ትምህርት ውጪ የሆኑ መጽሐፍትና ወረቀቶች፣ የእርሻ መሳሪያዎች እንዲሁም የተለያዩ ቀላልና ከባድ ብረታ ብረቶችን በሐራጅ ግልጽ ጨረታ ሽያጭ ዘዴ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም የሚከተሉ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል።

1. በጨረታው ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ተጫራች ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም የታደሰ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርበታል።

2. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ አስራ አምስት /15/ ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከደቡብ ኦሞ ዞን ከሣላ ማጎ ወረዳ ፋይናንስ /ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሮክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 በመምጣት የማይመለስ 100/አንድ መቶ/ የኢትዮጵያ ብር በመክፈል የዕቃዎችን ዝርዝር መረጃ እና መነሻ ዋጋ እንዲሁም የተጫራቾች መመሪያ የያዘ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ጨረታው 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 300 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን አስራ ስድስተኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በመቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 300 ላይ በሃና ከተማ ትም/ /ቤት አዳራሽ ይከፈታል።

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘውትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 230 እስከ 1130 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ዕቃዎችን በደ/ ዞን በሣላማጎ ወረዳ ሃና ከተማ በትም/ /ቤት፣ በግብርና /ቤት፣ በፋይንስ እና ፖሊስ /ቤት በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚገዙቱን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 20% /ሃያ በመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ በማዘጋጀት ከጨረታው መከፈቻ ቀደም ብሎ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች ተሸከርካሪዎችን በተመለከተ ቀደም ስል ያልተከፈለ የቦሎ እና የግብር ዕዳ ካለ በባለንብረት መስሪያ ቤቱ የሚሸፈን ሲሆን የስም ማዛወር የትራንዚት እና የጉሙሩክ ቀረጥ እና ሌሎች ወጭዎች ግን በገዥው የሚሸፈን ይሆናል።

6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉዋቸውን ንብረቶች ሙሉ ከፊያ ከፍለው እስከወስዱ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን ጠቅላላ ዋጋውን 20% /ሃያ በመቶ/ በማግስቱ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/ CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

7. የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከታወቀ ጀምሮ በአስራ አምስት የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበት ዋጋን በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁንና ሙሉ ከፊያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

8. መስሪያ ቤቱ የጨረታ ሰነዱን በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይደረጋል።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረቶች አጠቃለው 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ማንሳት ግዴታ ያለባቸው ሲሆን የማያነሱ ከሆነ ንብረቶቹ ለመንግስት ገቢ ውርስ ይሆናል።

10. /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡ስልክ ቁጥር 251- 916- 87-66-60 ወይም 251- 902-924-080

የደቡብ ኦሞ ዞን የሣላማጎ ወረዳ ፋይናንስ /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *