በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተተዉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 25, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የተተዉ ዕቃዎች የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ሐ‐10/2018

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት አስመጭዎች ዕቃቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተው የተቆጠሩ እና በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 10 መሠረት የተተዉ ንብረቶችን ማለትም

  • SKME IRON ADULI HAND WATCH, ANGLE, VALVE LED UFO HIGHBAY LIGHT,
  • WOODEN DOOR FRAME, MDF DOOR FRAME &
  • WATER PURIFIER HAIR FOLDABLE KID MINI LAPTOP TABLE,
  • RECHARGABLE HAIR BALL TRIMMER LINT REMOVER & ELECTRICAL SHOCK MOSQUITO KILLING LAMP,
  • MULTI- PURPOSE PRECISION SCREW DRIVER SET & MINI SCREW DRIVER SET WITH CASE, LED STRING LIGHTS:
  • CORRUGATED CARTON SHEET NON PRINTED RUBBER NAIL FILTER,S/S MANICURE SET,METAL DECORATIVE CROSS & EYE CLIPER OR S/S EYE LASH CURLER,
  • TV WALL MOUNT & S/S TVS HANGING BRACKET, LABORATORY STOOL CHAIR, WIRELESS BLUETOOTH EARPHONE GLASS MOBILE SCREEN PROTECTOR &
  • YAMAH ELECTRICAL GUITAR WITH CASE, BLADE FUSE, CKD MULTIMIDEA SPEAKERS AND OTHER ACESSORIES: SKD DISABLED ELECTRIC THREE WHEEL,ELECTRIC MOTOR CYCLE & OTHER እና S/S H HING & SWITCH BREAKER እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት በማስታወቂያ ሠሌዳ እና በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 መመልከት ይቻላል።

2. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።

3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ለሁሉም ዕቃዎች ዘርፉ በሚፈቅደው ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሽህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION አበባ፤ አዳማና ሞጆ MODO BRANCH OFFC በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፣አዳማ፣ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት።

4. የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን በዚሁ ዕለት ጠዋት 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ የሚከፈት ሆኖ ማንኛውም ተጫራች እስከ 4፡45 ሰዓት የሚጫረትበትን ዕቃ ለይቶ እቃ አወጋገድ ቡድን ቀርቦ ማስመዝገብ ይኖርበታል።

5 ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታውን ከአሸነፈ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም፤ የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

6. የሐራጅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት፡፡ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

7. በተራ ቁጥር 06 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል፡፡ ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።

8. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።

9.ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10.ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-90-94 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት