Your cart is currently empty!
ኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ (አ.ማ) የተለያዩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ባሉበት ሁኔታ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 26, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ክፍል 1
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ኢኢግ/ንአአኮ/ብግጨ/03/2018
ድርጅታችን ኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ (አ.ማ) በሰሩ በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪዎቸና ዋና መ/ቤት በንብረት ከፍል ተከማችተው የሚገኙ የምርት ግብዓትን ጨምሮ
- የተለያዩ የመበየጃ ኤሌክትሮዎች፣
- የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች፣
- የተለያዩ የእርሻ (የግብርና መሳሪያዎችና ትራክተሮች፣ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች፤
- የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ መለዋወጫ፣ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ የመበየጃ የመቁረጫ ማሽኖች እና ሞተር፣
- የተለያዩ ያገለገሎ ማምረቻ ማሽኖች፣ የተለያዩ የዩትሊቲ ዕቃዎች፣ የእጅ ማሽኖች፣ የኢንደስትሪያል አውቶ ኤሌትሪክ እና ኮንስትራክሽንና የቧንቧ መለዋወጫ፣
- የተለያዩ አነስተኛና ከባድ ተሽከርካሪ መኪናዎች መለዋወጫ፣ የተለያዩ የትራክተር ተቀፅላ መሳሪያዎች (implement spare} መለዋወጫ ዕቃዎች፣
- የተለያዩ ያገለገሉ ጀነሬተሮች፣ የተለያዩ የውሃ መርጫ (Try pole) እና PFC (power factor)፣ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችና መሳሪያዎች፣
- የተለያዩ ያገለገሉ በርሜሎችና ባትሪዎች እና ያገለገሉ አሮጌ ጎማዎች፣ የተለያዩ ኬሚካሎች፣ የተለያዩ የፕሮጀከት እቃዎች እና የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች የማሽን አካላት (rap) በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ ባሉበት ሁኔታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በጨረታ የሚወዳደሩት ተጫራቾች ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው፣ በዘርፉ የተሰማሩበት በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችላቸው ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣
- የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢነት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ኬሚካል ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለምን አገልግሎት እንደሚያውሉት ማረጋገጫ በፁሁፍ የሚያቀርቡና ኃላፊነት የሚወስዱ መሆን አለባቸው፡፡
- የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ካርድ ፓስፖርት መንጃ ፍቃድ ኦሪጅናልና ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ለጨረታ የሚያስፈልጉ ቅፆችን አዲስ አበባ ሜክሲኮ አደባባይ ከፈደራል ፖሊስ ዋና መ/ቤት ወደሳር ቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ በሚገኘው የኢትዩ ኢንጂነሪንግ ግሩፑ ዋና መስሪያ ቤት Block-A ቢሮ ቁጥር-001 የንብረት አስወጋጅ አብይ ኮሚቴ ቢሮ በመቅረብ የዕቃዎቹንና የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ከዚህ በታች አንቀጽ 4 በተመለከተው መሰረት የማይመለስ ብር 1000 በመከፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጠቀሱትን ሰነዶች በመግዛት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን ከሰነዱ ላይ በተጠቀሱት ቦታዎች በመሄድ መመልከት ይችላሉ፤
- ንብረቶቹን ካሉበት የግሩፑ ቦታ እስከ መዳረሻ ያሉ የትራንስፖርት ወጪ/ለማጓጓዣ፣ ለጫኝና አውራጅ፤ የመቆራረጫ፣ ለማስመዘንና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎች በገዥው ይሸፈናል፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ከሎት 01 እስከ ሎት 20 ድረስ ለተጠቀሱት ዕቃዎች ተጫራቹ በሚሰጠው ዋጋ መነሻነት 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ የኢትዩ ኢንጂነሪንግ ግሩፑ ዋና መስሪያ ቤት Block-A የንብረት አስወጋጅ አብይ ኮሚቴ ቢሮ ቁጥር-001 በሚገኝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተዘጋ በኋላ በራሱ ፍቃድ ከጨረታው ቢወጣ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ተወርሶ ለግሩፑ (ለኢኢግ) ገቢ ይደረጋል፡፡
- ጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለፁትን አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል፡፡ በእያንዳንዱ ሎት የተቀመጠውን ተጫራች በሚሰጠው ዋጋ መነሻነት 2 በመቶ (2%) ያላስያዘና በሰነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሜክሲኮ በሚገኘው የኢኢግ ዋና መስሪያ ቤት የ1ኛ ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ የእረፍት ወይም በዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
- በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ለግሩፑ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ግሩፑ ባወጣው ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድሩ ውድቅ ይሆናል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው 12 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃላይ በመክፈል ንብረቱን ከከፈሉበት አና ንብረቱን እንዲያነሱ ግሩፑ ከሚያወጣው ፕሮግራም ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማንሳት ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ጨረታው ከመዘጋቱ 5 ቀን በፊት በጽሁፍ ወይም በስልክ ቁጥር 09 86 33 33 55 ደውሎ ሻጭ መስሪያ ቤትን መጠየቅ ይችላሉ፡ የተጠየቀው ማብራሪያ የሚያስፈልገው መሆኑ ሲታመንበት የማስተካከያውን ማብራሪያ ሁሉም ተጫራጮች እንዲያውቁትና መጥተው እንዲወስዱ በመ/ቤቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ይለጥፋል፡፡
- ግሩፑ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ በህግ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማስታወሻ:
- ክፍያ የሚፈፀመው በኢትዮ–ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስም በተከፈተው ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1014900057975 እና አዋሽ ኢንተርናሸናል ባንክ ሂሳብ ቁጥር 01325662239600 መሰረት ይሆናል፡፡
- ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ አዲስ አበባ ከተማ (ሳሪስ ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ት/ት ቤት ጀርባ በሚገኘው የዋና መ/ቤት ስቶር፣ ገርጂ አምበሳ ጋራዥ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ፣ ሜክስኮ ጠማማ ፎቅ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ ሳሪስ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ ደብረ ብርሃን የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱሰትሪ (ሳሪስ፣ ሞጆ፣ ብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ (መካኒሳ(ባቱባ ሳሪስ)፣
- አዳማ የግብርና ማሽነሪ ኢንዱስትሪ (አዳማ) እና አቃቂ ቤዚከ ሜታልስ ኢንዳስትሪ ሲሆኑ ለበለጠ ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ሎት ጋር የተያያዙ ስለተጫረቱበት ዕቃ የሚገልፅ ተጨማሪ ማብራሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ ይኖራል፡፡
ከላይ ለተጠቀሰው አድራሻ:-
ሻጭ |
ኢትዮ–ኢንጂነሪንግ ግሩፕ |
በግሩፑ በኩል የተወከለው |
ንብረት አስወጋጅ አብይ ኮሚቴ |
የቢሮ ቁጥር |
Block-A ቢሮ ቁጥር 001 |
አድራሻ |
ሜክሲኮ ከፌደራል ፖሊስ ዋና መ/ቤት 300 ሜትር ዝቅ ብሎ |
ከተማ ክ/ከ |
አዲስ አበባ ሜክሲኮ ልደታ ክ/ ከ |
አገር |
ኢትዮጵያ |
ስልክ ቁጥር |
09 86 33 33 55 |
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ
cttx Agriculture and Farming cttx, cttx Aluminium Products cttx, cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Chemicals and Reagents cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Construction Machinery and Equipment cttx, cttx Disposal Sale cttx, cttx Electrical, cttx Energy, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Generators cttx, cttx Hand Tools and Workshop Equipment cttx, cttx Industrial Machinery Provision and Installation cttx, cttx Installation, cttx IT and Telecom cttx, cttx Machinery and Equipment cttx, cttx Mechanical cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Other Metals cttx, cttx Other Sales cttx, cttx Pumps, cttx Sales, cttx Sanitary and Ceramics cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Steel, cttx Steel Raw Materials and Products cttx, cttx Tri Wheeler, cttx Vehicle and Machinery Foreclosure cttx, cttx Vehicle and Machinery Sale cttx, cttx Water Engineering Machinery and Equipment cttx, cttx Water Pipes and Fittings cttx, Disposals and Foreclosure cttx, Electromechanical and Electronics cttx, Maintenance and Other Engineering Services cttx, Metals and Aluminium cttx, Motorcycles and Bicycles Purchase cttx, Motors and Compressors cttx, Power and Electricity cttx