ሰበታ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት ለሥልጠና አገልግሎት የሚውሉ ለሥልጠና የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 14, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

ሰበታ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2018 በጀት ዓመት ለሥልጠና አገልግሎት የሚውሉ

  1. የኮንስትራክሸን ዕቃዎች
  2. የኤሌክትሪክ እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  3. ለአውቶሞቲቭ ሥልጠና የሚውሉ ዕቃዎች
  4. የብረታብረት ሥልጠና የሚያገለግሉ ዕቃዎች
  5. ለልብስ ስፌት እና ቴክስታይል ማሠልጠኛ ዕቃዎች
  6. ለኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ ማሠልጠኛ ዕቃዎች እና
  7. የተለያዩ የቢሮ (የፈርኒቸር/Furniture) እቃዎች
  8. የዶሮ መኖ (የእንቁላል እና የቄብ ዶሮ)
  9.  የወተት ከብት መኖ
  10. ለሥልጠና የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ (Clearance) ማቅረብ የሚችሉ፤ አቅራቢዎች ዕቃውን ለማቅረብ የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።
  2. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ከኮሌጁ ፋይናንስ ክፍል ዘወትር በሥራ ሰዓት ለአንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰበታ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሂሳብ ቁጥር 1000016069225 በመክፈል መግዛት ይቻላል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ በተዘጋጀው ሰነድ ያቀረበውን ዋጋ (1%) በባንክ በተመሰከረለት CPO በሰበታ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚሸጡበትን ዋጋ በመጥቀስ በፖስታ በማሸግ በተባለው ቀን ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ ሞልተው የሚያቀርቡትን ዋናና ፎቶ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ስምና አድራሻ በማድረግ በድርጅቱ ማኅተም በማረጋገጥ ማቅረብ ይኖርበታል።
  6. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከለ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ቫትን (15%) ያካተተ መሆን አለበት።
  7. ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች ገቢ የሚሆነው አስፈላጊውን ጥራት ማሟላቱ በባለሙያ ሲረጋገጥ ይሆናል።
  9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ከስቶክ መሆን ይኖርበታል።
  10. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሁሉም የጨረታ ማስታወቂያ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ቀን 4:30 የሚከፈት ይሆናል።
  11. ከላይ የተገለጸው የመክፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል።
  12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ መረጃ በስስክ ቁጥር-0113383843/0113380022

የሰበታ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ