የሂሣብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን በእድሳት ምንክያት ንቃይ የእንጨት በሮች፤ የእንጨት ፓርቲሽኖች (አካፋይ)፣ የመፀዳጃ ቤት መቀመጫዎች፣ የእጅ መታጠቢያ ሲንኮች፣ የአሉሙኒየም በሮች፣ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ ሼልፎች፣ የወለል እምነበረድ፣ ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች፣ ላፕቶፕ ኮምፒዩተሮች፣ ፕሪንተሮች እና የመሳሰሉትን እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 18, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

መ/ቤታችን የሂሣብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን በእድሳት ምንክያት ንቃይ የእንጨት በሮች፤ የእንጨት ፓርቲሽኖች (አካፋይ)፤ የመፀዳጃ ቤት መቀመጫዎች የእጅ መታጠቢያ ሲንኮች፤ የአሉሙኒየም በሮች፤ ወንበሮች፤ ጠረጴዛዎች፣ ሼልፎች፤ የወለል እምነበረድ፣ ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች፣ ላፕቶፕ ኮምፒዩተሮች፣ ፕሪንተሮች እና የመሳሰሉትን ለሽያጭ በጨረታ ያቀረበ ስለሆነ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤

3. የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤

4. የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤

5. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000 (አስር ሺህ ብር) በ(Audit Service Corporation) ስም በሲ ፒ ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤

6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል 2ኛ ፎቅ ሂሳብ ክፍል በመቅረብ በኮርፖሬሽኑ የሥራ ቀንና ሰዓት (ቅዳሜና እና እሁድን ሳይጨምር) ጠዋት ከ2፡30 እስከ 6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡

7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍት ሆኖ የሚቆይ እና ጨረታው በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ በኮርፖሬሽኑ 1ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመቀበልም ሆነ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

9. ተጫራቾች በአካል በመቅረብ የሚሸጠውን ንብረቶች በመመልከት የጨረታ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ አድራሻ፡- ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካዛንችስ ከሲንቄ ባንክ ፊት ለፊት ወይም ከኦይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት ይገኛል።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 13 80 10 06 ወይም 09 13 16 65 04
መጠየቅ ይቻላል።
የሂሣብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን