ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የአሉሚኒየም ፓርትሽን አፍርሶ ባሉበት ሁኔታ እና ያገለገሉ የሞተር ዘይት በርሜሎች መግዛት ለሚፈልጉ ለሕጋዊ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Reporter(Oct 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ሕዳሴ ቴሌኮም

ያገለገሉ የአሉሚኒየም ፓርትሽን አፍርሶ ባሉበት ሁኔታ እና ያገለገሉ በርሜሎች መግዛት ለሚፈልጉ ሽያጭ

ግልጽ ጨረታ የጨረታ ቁጥር LT/HT/HO/11/2025

ሕዳሴ ቴሌኮም .ማ.

ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር / ለቢሮ አገልግሎት ሲጠቀምበት የነበረ የአሉሚኒየም ፓርትሽን አፍርሶ ባሉበት ሁኔታ እና ያገለገሉ የሞተር ዘይት በርሜሎች መግዛት ለሚፈልጉ ለሕጋዊ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል:: ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመፁበት ወቅት የንግድ ድርጅት ከሆኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃዳቸውን ዋናው እና ቅጅ፣ ግለሰብ ከሆኑ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም የመንጃ ፍቃድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች የሚገኙበት ቦታ የሕዳሴ ቴሌኮም . ደብረዘይት መንገድ ጠመንጃ ያዥ ባንክ ፊት ለፊት ከበእምነት ምግብ ቤት አጠገብ በሚገኘው ቤተሳይዳ ሕንጻ 2 እና 3 ፎቅ ቢሮ ያሉ ክፍሎች

  1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘዉን የጨረታ ሰነድ ከጥቅምት 13 ቀን 2018 . ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2:30-6:00 ከሰዓት 7: 30- 10:00 ቅዳሜ 230-500 ከቤተሳይዳ ሕንጻ 3 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ውጤቱ እንደታወቀ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) የባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.P.O/ ለሕዳሴ ቴሌኮም . በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ያገለገሉ ዕቃዎችን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ቩሑ አድራሻውን እና የጨረታውን ቁጥር በመጥቀስ ቤተሳይዳ ሕንጻ 3 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 ጥቅምት 24 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት የሚዘጋ ሆኖ በዕለቱ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 430 ሰዓት ቤተሳይዳ ሕንጻ 3 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 ይከፈታል።
  4. ተጫራቾች ጨረታውን በከፊል መጫረት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
  5. አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  6. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0968135675 ወይም 0968271291 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *