ኬኛ የግብርና መሣሪያዎች ማምረቻና ጠቅላላ ንግድ ኃላፊነቱ የተ/የግል ማህበር የተለያዩ መጠን ያላቸዉን ብረታ ብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ በኪሎ ግራም መሸጥ ይፈልጋል


Reporter(Oct 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2018

ኬኛ የግብርና መሣሪያዎች ማምረቻና ጠቅላላ ንግድ ኃላፊነቱ የተ የግል ማህበር የተለያዩ መጠን ያላቸዉን ብረታ ብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ በኪሎ ግራም መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶችን ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርቲፊኬት፤ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችልና የመንግሥት ግዴታ ስለመወጣቱ የሚያሳይ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸዉ።
  2. ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ 230-1100 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ 230-600 ሰዓት ድረስ ከግርጌ በተጠቀሰው አድራሻችን ቀርበው ከድርጅቱ ቢሮ የሀብት አስተዳደር መምሪያ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  3. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣ በኋላ 11ኛዉ ቀን 400 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 430 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን የጨረታዉ ቀን እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለዉ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
  4. የጨረታን ዋጋ በሌላ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ በህግ የተከለከለ ሲሆን ይህን ተላልፎ የተገኘ ከጫረታ ውጪ ይሆናል። ዋጋው ሲቀርብ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም።
  5. የጨረታውን ዋጋ ማቅረቢያ ኦሪጂናልና ኮፒውን በመለየት በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለበት። በሰም ያልታሸገ ፖስታ ተቀባይነት የለውም።
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ) የያዘ CPO ያስገቡበትን ለብቻ ወይም ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  7. የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው የጨረታው ማስከበሪያ እንደ አስፈላጊነቱ እንደ የስራ አፈጻጸም ዋስትና የሚታሰብለት ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታ አሸናፊው እንደታወቀ ይመለስላቸዋል።
  8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
  • አድራሻ፡ አ.አ ቦሌ /ከተማ ወረዳ 02 ስልክ ቁጥር 011 614-9253/09 32-12-60-57/09 11-09-61-11
  • ጃፓን ኤምባሲ አካባቢ ራማዳ ሆቴል ፊት ለፊት ስንታየሁ በላይ ህንፃ 6 ፎቅ ኬኛ የገብርና መሣሪያዎች ማምረቻና ጠቅላላ ንግድ ኃላፊነቱ የተ/የግል ማህበር