Your cart is currently empty!
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሲዳማ ሪጅን የተለያዩ ያገለገሉ ለተቋሙ አገልግሎት መስጠት የማይችሉ ብረታብረቶች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቅያ
ቁጥር፦ EEU/S/R/S/M/D/B/002/2018
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሲዳማ ሪጅን የተለያዩ ያገለገሉ ለተቋሙ አገልግሎት መስጠት የማይችሉ ብረታብረቶች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የሚወደው ንብረት |
የሚገኘበት ቦታ |
መለኪያ
|
ብዛት
|
የጨረታ ማስከበሪያ CPO/ |
የጨረታ መዝጊያ |
የጨረታ መክፈቻ |
|
1 |
የማያገለግሉ ብረታ ብረቶች |
ሲዳማ ሪጅን ዕቃ ግምጃ ቤት ሐዋሳ) |
በኪ.ግ |
20,000 |
50,000
|
ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 |
ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 |
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በድርጅታችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000182117742 EEU_SOUTHRN አካውንት ቁጥር በኢ/ኤ/አገ/ ሲዳማ ሪጅን ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁE 1000182117742 የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) ግቢ በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት በሐዋሳ ከተማ አሮጌው መነኸሪያ አጠገብ በሚገኘው በድርጅቱ ቢሮ የኢ/ኤ/አዝ/ ሲዳማ ሪጅን ፋይናንስ ቢሮ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 405 በመምጣት የሚወገደውን ንብረት ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዘወትር በሥራ ቀናት (ከሰኞ እስከ አርብ) ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ፣ ከሰአት 7፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቱ በሚገኙበት ሲዳማ ሪጅን ዕቃ በግምጃ ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /Bid Security/ ማስያዝ ይኖርባቸውል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ ስማቸውን በመግለጽ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ድረስ ብቻ በሲዳማ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባይገኙም በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሲዳማ ሪጅን የሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205 ይከፈታል።
- ተጨማሪ ማብሪሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0462121972/0462121970 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች በጨረታው የተጠቀሰው ብዛት ቢጨምር/ቢቀንስ/ የመረከብ ግዴታ አለባቸው።
- ጨረታውን የሚወዳደሩ የሀገር ውስጥ አምራቾች ብቻ መሆነ ያለባቸው ሲሆን ከኢንዱስትሪ ሚንስቴር የተሰጣቸው አምራችነት ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሲዳማ ሪጅን
cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Construction Machinery and Equipment cttx, cttx Disposal Sale cttx, cttx Metal and Metal Working cttx, cttx Other Metals cttx, cttx Other Sales cttx, cttx Sales, cttx Steel, cttx Steel Raw Materials and Products cttx, Disposals and Foreclosure cttx, Metals and Aluminium cttx