Your cart is currently empty!
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ያገለገሉ የብረት፣ የእንጨት፣ የፕላስቲክ እና ተሽከርካሪ ወንበሮች እንዲሁም የጠረጴዛ እና የሸልፍ ግንጣይ በጅምላ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 31, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ያገለገሉ የብረት፣ የእንጨት፣ የፕላስቲክ እና ተሽከርካሪ ወንበሮች እንዲሁም የጠረጴዛ እና የሸልፍ ግንጣይ በጅምላ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ያገለገሉ የብረት፣ የእንጨት፣ የፕላስቲክ እና ተሽከርካሪ ወንበሮች እንዲሁም የጠረጴዛ እና የሸልፍ ግንጣይ በጅምላ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በሽያጭ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተጫራቾች መስፈርት የማክበርና የመፈፀም ግዴታ አለባቸው።
1. ይህ ጨረታ ድርጅት ወይም ግለሰብ ሊሳተፍበት ይችላል።
2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ሙሉ ቀን እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ሙሉቀን እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ባሉት የሥራ ቀናት ጠዋት 3፡00 እስከ 6፡00 ከሰዓት ከ 7፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ቃሊቲ ቶታል አካባቢ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ ቋሚ ግምጃ ቤት እና ወርቁ ሰፈር በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
4. አንድ ተጫራች ያገለገሉ የብረት፣ የእንጨት፣ የፕላስቲክ እና ተሽከርካሪ ወንበሮች እንዲሁም የጠረጴዛ እና የሸልፍ ግንጣይ በጅምላ የሚገዛበትን ጥቅል ዋጋ በማስቀመጥ መጫረት ይኖርበታል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ሲገዙ ትክክለኛ አድራሻቸውንና ሥማቸውን በመግለጽ ፈርመው መውሰድ አለባቸው።
6. ጨረታው ኅዳር 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው (በዕለቱ) በ4፡30 (አራት ሰዓት ተኩል) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።
7. ኢንተርፕራዙ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር የመታወቂያ እና የጨረታ ሠነድ የገዙበትን ደረሰኝ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ማሳሰቢያ፡– ለሽያጭ የቀረቡት የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ የብረት ፣ የእንጨት ፣ የፕላስቲክ እና ተሽከርካሪ ወንበሮች እንዲሁም የጠረጴዛ እና የሸልፍ ግንጣይ ፡–
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቃሊቲ ግቢ ስልክ ቁጥር 011-440-3434
ማዞሪያ 011-442-2270/71/72
E-mail አድራሻ info@dce-et.com
የድረ–ገጽ አድራሻ WWW.dce-et.com
ፖ.ሳ.ቁ. 3414 / 11 440-4071/011 442-0746
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ