የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጎተራ በሚገኘው ግቢ ውስጥ ያሉትን የተለያየ ብረታ ብረቶችንና ጎተራ (Silo) ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Jan 30, 2026)

ጨረታ ማስታወቂያ

ኮርፖሬሽናችን ጎተራ በሚገኘው ግቢ ውስጥ ያሉትን የተለያየ ብረታ ብረቶችንና ጎተራ (Silo) ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው።

  1. ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውንና የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 1000 ብር /አንድ ሺህ/ በመክፈል ከጥር 20 ቀን 2018 . እስከ የካቲት 11 ቀን 2018 . ዘወትር ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ከዋናው /ቤት /አዲስ አበባ/ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 230 -630 እንዲሁም ከሠዓት 730 -1100 እና ቅዳሜ 230 እስከ 630 ሠዓት መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ የካቲት 11 ቀን 2018 . ከጧቱ 430 ሠዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ንብረት 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ሲሞሉ በግልጽ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ማሳየት አለባቸው።
  5. ጨረታው የካቲት 11 ቀን 2018 . ከጧቱ 430 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጧቱ 430 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው /ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  6. የጨረታው አሸናፊ ተጫራች በጨረታው ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ክፍያ 15 /አሥራ አምስት/ የሥራ ቀናት ውስጥ በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል። በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሳ 15ኛው ቀን በኋላ ላላነሳበት ቀን በየቀኑ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ቅጣት የሚከፍል ይሆናል።
  7. አሸናፊው በራሱ ወጪ የተለያዩ ብረታ ብረቶችንና የእህል ማከማቻ የነበረ ጎተራ (Silo) መንቀል ማስጫንና ማጓጓዝ ይኖርበታል።
  8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 416-3483 መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ፡በቅሎ ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር 011 416 3483 

አዲስ አበባኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *