Your cart is currently empty!
የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አከሲዮን ማህበር የተለያዩ ዕቃዎች በዝግ ጨረታ መሠረት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 08, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 032/2018
የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አከሲዮን ማህበር ዝርዝራቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በዝግ ጨረታ መሠረት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- የተለያየ መጠን ያላቸው የተጠናቀቁ የጨርቅ ተረፈ ምርቶች
- የተለያየ አይነት የጥጥ ቅሪቶችና ተረፈ ምርቶች
- የተለያዩ አይነት ብረታ ብረት እና መለዋወጫ ዕቃዎች
- የተለያየ መጠን ያላቸው የተጋቡ የፕላስቲክ ጀሪካኖችና የብረት በርሜሎች እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎች በጨረታው ማንኛውም በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው ግለሰብ ወይም ድርጅት መሣተፍ የሚችል ሲሆን ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከአከሲዮን ማህበሩ ቅ/ጽ/ቤት አዲስ አበባ ወይም ከዋናው መ/ቤት ኮምቦልቻ መግዛት ይችላሉ፡፡
ዕቃዎቹን ዘወትር በስራ ሰአት (ከሰኞ – አርብ ከ 2፡00-10፡00 እና ቅዳሜ ከ 2፡00-6፡00) ዋናው መ/ቤት ኮምቦልቻ በመመልከት የሚገዙበትበን ነጠላ ዋጋ አ/ማህበሩ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በትክክል በመሙላት በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በጨረታ መመሪያው ላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በ (CPO) በማስያዝ ከላይ በተገለጹት ቦታዎች ላይ በመገኘት ዋጋ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ጨረታው ማስታወቂያው በተዘጋበ 3ኛውቀን ኮምቦልቻ /ወሎ/ በሚገኘው በዋናው መ/ቤት ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
አ/ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ
ስልክ ቁጥር 033-5510627/ 5510211(ኮምቦልቻ)
ስልክ ቁጥር 011-5511805 / 5530124 (አዲስ አበባ)
ራስ ደስታ ዳምጠው ገዳና ፓፓሲኖስ ህንጻ 1ኛ ፎቅ
ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ
አክሲዮን ማህበር