Your cart is currently empty!
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 11, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር MS/LP/02/2026
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፀው ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
|
1 |
ቁርጥራጭ ብረታ ብረት |
ኪ.ግ |
+750000 |
- ከላይ በዝርዝር የቀረቡትን ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት ዕቃዎች ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሳተፍ የምትፈልጉ በዘርፉ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሠርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሠርተፊኬት በማቅረብ የማይመለስ ብር 300(ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ሜክሲኮ ፊሊፕስ ህንፃ ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 215 ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ገዝተው በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ፤
- ማንኛውም ተጫራች መግዛት የሚፈልገውን ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት ዕቃዎችን መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ንብረት አስተዳደር ቡድን በግንባር በመቅረብ መመልከት ይችላል፣
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሠርተፊኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 500,000.00 (አምስት በመቶ ሺህ ብር) በባንክ ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማስያዝ አለባቸው፣
- ተጫራቾች፣ ከዚህ የጨረታ ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ዝርዝር ላይ የሚሰጡትን ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በትክከል በመሙላት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በታሽገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ በላዩ ላይ ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ4፡30 ሰዓት በፊት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 119 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ ከዚህ ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ተ.እ.ታ (VAT) የማይጨምር ሲሆን፣ የጨረታ አሸናፊዎች ለሚገዙት ዕቃ ተጨማሪ እሴት ታክስ የመክፈል ግዴታ አለባቸው፣ ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ይኸው እንደተገለጸላቸው ያሸነፉበትን ሙሉ ዋጋ በቅድሚያ በመክፈል ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለጸበት ቀን አንስቶ 30(ሰላሳ) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ ሲኖርባቸው፤ ይህ ባይሆን ግን ድርጅቱ ጨረታውን ሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያነት የተያዘውን ገንዘብ ለራሱ ገቢ የሚያደርግ መሆኑን ከወዲሁ ያሳውቃል፣
- ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ላይ ከላይ ከፍ ብሎ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 119 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
- ፋብሪካው ስለ አሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡ 0115 -50567, 0115-505633
ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ሕንፃ
አዲስ አበባ
መተሐራ ስኳር ፋብሪካ