Be'kur (Apr 15, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕ/ጉጃም ዞን የቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በቡሬ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ንብረት ክፍል የሚገኘውን የተለያዩ ብረታ ብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. ተጫራቾች የሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 200‚000 (ሁለት መቶ ሽህ) ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
4. የታደሰ የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁጥር ከ1-4 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ዋናውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. የጨረታ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኛሉ ሆኖም ግን ብረታ ብረቶቹን በአካል ማየት ከፈለጉ ቡሬ /ዙ/ወ/ ግብርና ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ማግኘት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከመጋቢት 28/2018 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወጥ በሆነ በታሸገ ፖስታ ዋና እና ፎቶ ኮፒው ቡ/ዙ/ወ/ገ/ ጽ/ቤት ግዥ/ን/አስ/ ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ታሽጐ 4፡30 ጨረታው ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሠረት የአንዱን ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ድምር በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመውሰድ ብር 200 (ሁለት መቶ ) በመክፈል ሰነዱን ቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ግዥ/ን/አስ/ ቡድን መውሰድ ይችላሉ፡፡
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
14. በጨረታ ማስታወቂያው ያልተካተቱ ሃሳቦች በግዥ መመሪያው ቁጥር 1/2003 እና በሌሎች በተሻሻሉ የግንባታ የግዥ መመሪያዎችን የሚገዙ ይሆናል፡፡
15. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ/ን/አስ/ ቡድን በአካል በመገኘት በስልክ ወይም ቁጥር 058 774 0237 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት