Be'kur (Apr 13, 2026)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሴ/መ/ቤቶች እስቶር ውስጥ የሚገኝ 1ኛ አሮጌ የቴዮታ መኪና ጎማ፣ 2ኛ አሮጌ የቴዮታ መኪና ባትሪ እና 3ኛ አሮጌ የብረት በርሚል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
1. ማንኛውም ግለሰብ መወዳደር ይችላል።
2. መነሻ ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
3. የዕቃ አይነትና ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት ብር) በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 8 በመቶ ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ማለትም በአማረኛ የተተረጎመ፣ ሲፒኦ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው ከሚያዚያ 05/2018 ዓ/ም እስከ ሚያዚያ 19/2018 ዓ/ም ድረስ ይውላል።
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ቀናት ከሚያዚያ 05/2018 ዓ/ም እስከ ሚያዚ 19/2018 ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 ሚያዚያ 20/2018 ዓ/ም 8፡00 ታሽጎ 8፡15 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኝም ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም።
9. ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር (በሎት) ምድብ ይሆናል።
10. ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ፓራፍ ይደረግበት።
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጃ/ወ/ከአራቱ ንብረት ክፍል ሲሆን አጠቃላይ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሲሆን እቃውን መውሰድ ይችላሉ።
13. ተጫራቾች ትራንስፖርት እንዲሁም ማውረጃና መጫኛ አስበው መሙላት አለባቸው፡፡ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት