የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በየእለቱ ከሚታረዱ ከዳልጋ ከብት የሚገኘውን እርጥብ ቆዳና ከበጎች እና የፍየሎች የሚገኘው እርጥብ ሌጦ፣ የስጋና አጥንት መኖ፣ የዳልጋ ከብት ቀንድ እና ለሳሙና መስሪያ ግብዓት የሚሆነውን የተነጠረ ሞራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በየእለቱ ከሚታረዱ ከዳልጋ ከብት የሚገኘውን እርጥብ ቆዳና ከበጎች እና የፍየሎች የሚገኘው እርጥብ ሌጦ፣ የስጋና አጥንት መኖ፣ የዳልጋ ከብት ቀንድ እና ለሳሙና መስሪያ ግብዓት የሚሆነውን የተነጠረ ሞራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Apr 22, 2026)

የተረፈ ምርት ሽያጭ

ጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከግንቦት 01   2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓም ለሚያመርተው በየእለቱ ከሚታረዱ ከዳልጋ ከብት የሚገኘውን እርጥብ ቆዳና ከበጎች እና የፍየሎች የሚገኘው እርጥብ ሌጦ፣  የስጋና አጥንት መኖ፣ የዳልጋ ከብት ቀንድ እና ለሳሙና መስሪያ ግብዓት የሚሆነውን የተነጠረ ሞራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች፡

  • በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ ስርተፍኬት ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ ማስረጃ ኮፒ ማያያዝ አለበት።
  • የጨረታ ማስከበሪያን በተመለከተ ለዳልጋ ከብት የጨረታ ማስክበሪያን የሚሆን ለሦስት የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) እና በወር ውስጥ ለሚገኝው የበግና ፍየል ሌጦ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) የዳልጋ ከብት ቆዳ ጨረታ ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች የቅድመ ክፍያ 10 ቀናት ብር 4,000,000.00 (አራት ሚሊዮን ብር) እና የበግና ፍየል ሌጦ ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች የቅድመ ክፍያ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በሲ.. ብቻ ማስያዝ ይኖርባታል።
  • ለስጋና አጥንት መኖ ለሦስቱ የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ለዳልጋ ከብት ቀንድ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) እና ለተነጠረ ሞራ ለሦስቱ የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።
  • ጨረታውን ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች ለዳልጋ ከብት ቀንድ ምርቱን በሳምንት ሁለት ቀን እንዲሁም ለስጋና አጥንት መኖ ምርቱ በሚመረትበት በሳምንት ሦስት ቀን (ሰኞ ማክሰኞ እና ሐሙስ) እና ለተነጠረ ሞራ ምርቱ በተመረተበት ቀን ሙሉ በሙሉ የእጅ በእጅ ሽያጭ በማከናወን ማንሳት የሚችል መሆን አለበት።
  • ምርቱን ለመግዛት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች በጨረታ መመሪያ ላይ በተገለፀው መሰረት ይሆናል።
  • አሸናፊው የሚኖረው መብትና ግዴታዎች በውል ውስጥ የሚካተት ይሆናል።
  • ከቆዳና ሌጦ ውጪ ላሉት ምርቶች የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይቻላል።
  • ጨረታው ለዳልጋ ከብት ቆዳ እና ለበጎች እና ፍየሎች እርጥብ ሌጦ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓም፣ ለስጋና አጥንት መኖ ሚያዝያ 22 ቀን 2018 .. ለዳልጋ ከብት ቀንድ ሚያዝያ 26 ቀን 2018 . እና ለተነጠረ ሞራ ሚያዝያ 29 ቀን 2018 . በተመሳሳይ ሰዓት 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 141 63978 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ:።

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *