አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ በግጭት እና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸው ለደንበኞች የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል 9 ተሽከርካሪዎችን፣ 18 የተሽከርካሪ ጋቢናዎች፣ የተለወጡ አሮጌ የተሽከርካሪ ዕቃዎች (ቅሪተ አካሎች)፣ 55 ከረጢት የዶሮ መኖ እና 1 የውሃ ታንከር በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ በግጭት እና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸው ለደንበኞች የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል 9 ተሽከርካሪዎችን፣ 18 የተሽከርካሪ ጋቢናዎች፣ የተለወጡ አሮጌ የተሽከርካሪ ዕቃዎች (ቅሪተ አካሎች)፣ 55 ከረጢት የዶሮ መኖ እና 1 የውሃ ታንከር በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 25, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ በግጭት እና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸው ለደንበኞች የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል 9 ተሽከርካሪዎችን፣ 18 የተሸከርካሪ ጋቢናዎች፣ የተለወጡ አሮጌ የተሽከርካሪ ዕቃዎች (ቅሪተ አካሎች) 55 ከረጢት የዶሮ መኖ እና 1 የውሃ ታንከር በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

1. የመኪናዎቹን ንብረቶቹን ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 22 ቀን 2018 . ከቀኑ 1000 ሰዓት ድረስ ተሸከርካሪዎቹን/ንብረቶቹን ቀጥሎ በተጠቀሰው አድራሻ በስራ ሰዓት ማየት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1.1 አፍሪካ ኢንሹራንስ ጉዳት የደረሰባቸው ተሽከርካሪዎች ማቆሚያ ቦታ ቃሊቲ ኖክ ማደያ በሚድሮክ ተርሚናል ወደ ውስጥ 1.5 ኪሜ ገባ ብሎ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች ማቆሚያ ቅጥር ግቢ ውስጥ።

2. ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀው እና የተሽከርካሪዎቹን ንብረቶቹን ዝርዝር የያዘውን ፎርም ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 22 NB ቢዝነስ ሴንተር 6 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 እና በኩባንያው ሪከቨሪ ቅጥር ግቢ ውስጥ እስከ ሚያዚያ 22 ቀን 2018 . 1100 ሰዓት ድረስ የማይመለስ 100.00 ብር በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይቻላል።

3. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን እያንዳንዱን ተሽከርካሪ /ንብረት ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ሚያዚያ 22 ቀን 2018 . ከቀኑ 1100 ሰዓት ድረስ 22 NB ቢዝነስ ሴንተር 6 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ተሽከርካሪ/ንብረት የመነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን ይህን መስፈርት የማያሟላ ተጫራች ወዲያውኑ ከጨረታው ይሰረዛል።ተጫራቹ በጨረታው ከተሸነፈ በማስያዣ ያስያዘው ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ የሚጫረቱበት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት፡፡

6. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት በራሳቸው ስም ከፍለው እንዲወስዱ ይደረጋል። ግዥውን ለሌላ ሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ የማይፈቀድ መሆኑን እየገለጽን ይህ ካልሆነ ግን አሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከቢሪያ (CPO) በቅጣት መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል።

7.ጨረታው ሚያዚያ 24 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ቦሌ አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ ዋና /ቤት ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል።

8.ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪ / ንብረት ሙሉ ክፍያ 15% VAT ጨምሮ 7 የስራ ቀናት ውስጥ በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል። ሙሉ ክፍያ ፈጽመው በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ለአስር ተከታታይ ቀናት በየቀኑ ብር 100.00 አንድ መቶ የማቆሚያ ቦታ ኪራይ የምናስከፍል ሲሆን 10 ቀናት ውስጥ ካላነሱ ግን ያስያዙት ገንዘብ በቅጣት መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል፡፡

9.ለጨረታ በቀረቡት ተሸከርካሪዎች ንብረቶች ላይ የሚፈለጉ የስም ማዛወሪያ፣ ግብርና ልዩ ልዩ ወጪዎች ቢኖሩ በጨረታው አሸናፊ የሚሸፈን ይሆናል፡፡

10.ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911-21-89-95 011-6-18-08-43 በመደወል ወይም ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግንባር ቀርቦ መረዳት ይቻላል፡፡

11./ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ (ኢማ) ከእንደራስ ናሽናል ጋር በመተባበር

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *