በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ያገለገሉ ያማሃ ሞተር ሳይክሎችና ቶዮታ ፒካፕ መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ያገለገሉ ያማሃ ሞተር ሳይክሎችና ቶዮታ ፒካፕ መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (May 12, 2026)

በድጋሚ የወጣ ያገለገሉ ዕቃዎች

ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት /ቤት ያገለገሉ ያማሃ ሞተር ሳይክሎችና ቶዮታ ፒካፕ መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡

በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ወይም ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት የሚፈልጉ ግለሰቦች፣ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከመ/ቤታችን ግዥ ክፍል የማይመለስ ብር 200 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 5% የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ሂሳብ ማዘዣ CPO ብቻ በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

ሁሉም ተጫራች የጨረታ ዋጋ ከመሙላቱ አስቀድሞ ተሽከርካሪዎች ያሉበትን ደረጃ በመ/ቤታችን ቅጥር ግቢ በአካል ቀርቦ ማየት አለባቸው። ሳያዩ ዋጋ ሞልተው በኋላ ሌላ ጭቅጭቅ መግባት ተገቢ ያለመሆኑን መገንዘብ አስፈላጊ ይሆናል።

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ቆይቶ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 500 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ 800 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ሳይሆን ከቀረ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ሂደቱ ይከናወናል።

ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ያሸነፈውን ገንዘብ በባንክ አካውንታችን ላይ አጠቃሎ በመክፈል 5 የሥራ ቀን ውስጥ ተሽከርካሪዎችን ማንሳት አለበት። በተባለው 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ገንዘብ ከፍሎ ዕቃውን ባያነሳ የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ተደርጎ የጨረታ አሸናፊነቱ ይሰረዛል።

/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻአርባ ምንጭ ከተማ ከትልቁ ማዘጋጃ ከፍ ብለው በትልቁ ሕንፃችን እንገኛለን

ስልክ 0046 181-4091 / 09-83-26-16-48

የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ማት /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *