የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጎንደር ሪጅን ብረታ ብረቶችን፣ አሮጌ ጎማዎች፣ አሮጌ ምሶሶዎች፣ ባዶ በርሜሎች፣ አሮጌ ትራንስፎርመሮች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጎንደር ሪጅን ብረታ ብረቶችን፣ አሮጌ ጎማዎች፣ አሮጌ ምሶሶዎች፣ ባዶ በርሜሎች፣ አሮጌ ትራንስፎርመሮች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (May 13, 2026)

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/ጎ/ሪ/ግ/ጨ/004/2018

የኢትዮጵያ ኤሌከትሪክ አገልግሎት ጎንደር ሪጅን ንብረቶች የሆኑ ብረታ ብረቶችን፤ አሮጌ ጎማዎች፣ አሮጌ ምሶሶዎች፤ባዶ በርሜሎች፣ አሮጌ ትራንስፎርመሮች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

.

 

የዕቃው አይነት

 

ሎት

 

የሚገኝበት ቦታ

 

የጨረታ ማስከበሪያ (CPO)

የጨረታ መዝጊያ ቀን

 

የጨረታ መክፈቻ ቀን

 

1

ብረቶች (ክሮስ አርም፤ታይ ስትራፐ፤ የድራም ብረቶች፣ አልሙንየም ሽቦዎች

ሎት-1

 

ጎንደር ልደታ ስብስቴሽን

 

50,000.00

 

ግንቦት 17 ቀን 2018 . ከቀኑ 8:00

 

ግንቦት 17 ቀን 2018 . ከቀኑ 8:30

 

2

አሮጌ ምሶሶ

3

አሮጌ ጎማዎች

 

አሮጌ የመኪና ባትሪዎች

4

አሮጌ በርሜሎች

1

አሮጌ ትራንስፎርመሮች

 

ሎት-2

 

ጎንደር ልደታ ስብስቴሽን

 

50,000.00

 

ግንቦት 17 ቀን 2018 . ከቀኑ 8:30

ግንቦት 17 ቀን 2018 . ከቀኑ 8:30

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ። ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በድርጅታችን አካውንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር (Gondar Region Electric Utility account 1000257403657) የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ/ ገቢ በማድረግ ዘወትር በስራ ስዓት ጎንደር ከተማ ማህበረ ቅዱሳን ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር፡-304 ጎንደር ሪጅን ሰፕላይ ቸይን፤ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ በመምጣት የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

1. ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዘወትር በስራ ቀናት ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን፣ እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ስማቸውን እና ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

4. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ጎንደር ከተማ ማህበረ ቅዱሳን ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር፡-304 ጎንደር ሪጅን ሰፕላይ ቸይን፣ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ በሚገኘው ቢሮ ይከፈታል።

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ መሆን አለበት።

6. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር +251 58 211-6536 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጎንደር ሪጅን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *