Addis Zemen (May 23, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 24/2018
በኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኮስሞቲክስ ዘርፍ ዕቃዎች፣ አልባሳት ዘርፍ እቃዎች፣ የንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች፣ ኤልክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች እና ልዩልዩ ዘርፍ እቃዎች በግልጽ ጨረታ እንዲሁም አልባሳት ዘርፍ እቃዎች፣ ልዩልዩ ዘርፍ እቃዎች፣ ጌጣጌጥ ዘርፍ እቃዎች እና ስፔርፓርት ዘርፍ እቃዎች በሀራጅ ጨረታ በጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 24/2018 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ያለበት ሲሆን በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው ለሀራጅ ጨረታ በጨረታ መክፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
2. ከላይ በተራ ቁጥር አንድ የተገለጸው ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም እንዲሁም የሚሸጠው እቃ ተሽከርካሪ ሲሆን የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል፡፡
3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) በቀጥታ አካውንት ቁጥር 1000296553216 በጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ፣ በተራ ቁጥር 1 ከተገለጹት እና ሌሎች መረጃዎች ጋር በማያያዝ በፖስታ የተጫራቹን ስም እና ፊርማ በግልጽ በመጻፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን 20/09/2018 ዒ.ም ጠዋት 3፡30 ድረስ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡
4. በሀራጅ ጨረታ ለወጡት እቃዎች ለመሳተፍ ለአልባሳት ዘርፍ እቃዎች ብር 51,000 (ሃምሳ አንድ ሺ ብር)፣ ለልዩልዩ ዘርፍ እቃዎች ብር 15,500 (አስራ አምስት ሺ አምስት መቶ ብር)፣ ለጌጣጌጥ ዘርፍ እቃዎች ብር 1,502 (አንድ ሺ አምስት መቶ ሁለት ብር) እና ለስፔርፓርት ዘርፍ እቃዎች ብር 5,000 (አምስት ሺ ብር) ለየብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO በቀጥታ አካውንት ቁጥር 1000296553216 በጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት የጨረታ ሰነዱን እና በተራ ቁጥር አንድ የተገለጹትን መረጃዎች በመያዝ በቀን 20/09/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ላይ መገኘት አለባቸው፡፡
5. ከላይ በተራ ቁጥር 3 እና 4 በተገለጸው መሰረት በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች መወዳደር ወይም መጫረት አይችልም፡፡
6. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሳጥኑ ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ራሱን ከውድድር ውጭ ማድረግ አይቻልም፡፡
7. ለግልጽ ጨረታ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ9፡00-12፡00 የእቃዎቹን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100፡00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20/09/2018 ጠዋት 3፡00 ድረስ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 መግዛት ይችላሉ፡፡
9. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች ለናሙና ዕይታ የሚቀርቡበት ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ግንቦት 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 20/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2፡00 6፡30 ሰዓት ከሰዓት በኃላ ከ9፡00-12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት 2፡00-6፡00 ሰዓት የእቃዎቹን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፡፡
10. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ
|
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም
|
የጨረታው አይነት
|
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ
|
የጨረታው መዝጊያ እና መከፈቻ ቀንና ሰዓት
|
|
1 |
ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
|
ግልጽ ጨረታ
|
እስከ 20/09/2018 ከጠዋት 3፡30 ሰዓት
|
በ20/09/2018ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ተዘግቶ በእለቱ 3፡40 ሰዓት ይከፈታል
|
|
2 |
ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
|
ሀራጅ ጨረታ
|
እስከ 20/09/2018 ከጠዋት 3፡30 ሰዓት
|
በ20/09/2018ዓ.ም ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ይከፈታል
|
11. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በጋላፊ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቦታው ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱ ማስረጃዎች ኦርጂናል ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
12. በጨረታ ለሚሸጥ እቃ የጨረታ ውጤት እንደተገለጸ ከአሸናፊው ጋር የሽያጭ ውል እንደተደረገ ይቆጠራል፡፡
13. ምድብ ለወጣላቸው ሀራጅ እቃዎች ጨረታው የሚካሄደው በምድብ ሲሆን ተጫራቾች አሸናፊ የሚያደርጋቸው ለምድቡ ባቀረቡት የእያንዳንዱ እቃዎች ዋጋ ድምር ከፍተኛው ዋጋ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች በምድቡ ለቀረቡት ለእያንዳንዱ እቃዎች ዋጋ መስጠት አለባቸው፡፡
14. ተጫራቾች ከአሸነፉበት የእቃ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) የሚጨመር ይሆናል፡፡
15. ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
16. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን ባሉበት ቦታ እና ሁኔታ የመረከብ እና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይችላል፡፡
17. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ05 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመስሪያቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሜ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን አሸናፊው የአሸነፈበትን የእቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል፡፡ ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል፡፡
18.በጨረታ የሚሸጠው እቃ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከመወረሱ በፊት የእቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፡፡
19. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች የሚገኙበት ቦታ ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት መሆኑ ይታወቅ፡፡
20. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ውርስ መጋዘን አስተደደር የስራ ሂደት ልክ ቁጥር 033-559-0114 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት