Addis Zemen (Jun 04, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 001/2018
የቅ/ጽ/ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት፤የተለያዩ ያገለገሉ የተሽከሪካሪ አካላት እና መለዋወጫ ዕቃዎች ፤የተለያዩ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እንዲሁም የተለያዩ ያገለገሉ ፕላስቲክ ወንበሮች ባሉበት የጨረታ ሽያጭ
- ሎት 1. የተለያዩ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ሽያጭ፤
- ሎት 2 የተለያዩ ያገለገሉ የመኪና ጎማ፣ ያገለገሉ ባትሪ እና ያገለገሉ የመኪና ዕቃዎች/ ብረት/ ሽያጭ
- ሎት 3.ያገለገሉና የተሰባበሩ ፕላስቲክ ወንበሮች ሽያጭ
ስለሆነም ተወዳዳሪዎች/ተጫራቾች ፡–
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የአቅራቢነት ዝርዝር በዌብሳይት ላይ የተመዘገቡበት ወረቀት (በቅርብ ጊዜ ፕሪንት የተደረገ)፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ግብር ከሚከፈልበት መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የምዝገባ ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መቐለ ጉምሩክ ኮሚሽን ኤስኤስ ማዞሪያ ቢሮ ቁጥር 301 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 2% ወይም ብር 2,000.00 /ሁለት ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ቢድ ቦንድ /BID BOND/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚገዙት ንብረት ባሸነፉት ዕቃ ላይ 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና በስማቸው በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አቅራቢዎች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገፅ ፊርማ እና የድርጅቱን ማህተም በመምታት ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ በቅ/ፅ/ቤታችን ስም የጨረታ ቁጥሩን እና የግዥውን አይነት በመግለጽ በኤንቨሎፕ ላይ በመጻፍ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዚሁ ቀን 4፡00 ሰአት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡15 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል ።ነገር ግን የመክፈቻው ቀን እሁድ ወይም የበአል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ለአሸናፊ ተወዳዳሪዎች በጨረታው ማሸነፋቸው እንደተገለጸላቸው ቅሬታ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ቅሬታቸውን በጽሑፍ ለቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ በ5 ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላሉ፡፡በውድድሩ የቀረበ ቅሬታ ከሌለ አሸናፊ ድርጅቶች በ15 ቀናት ውስጥ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ቀርበው ግዥውን ከሚፈፅመው አካል ጋር ውል ይፈፅማሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠመረጃ ስልክ ቁጥር፡-0942-603-608/0914754-940 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡– በጉምሩክ ኮሚሽን የመቐለ ቅ/ፅ/ቤት ኤስኤስ ማዞሪያ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301
በጉምሩክ ኮሚሽን የመቐለ ቅ/ጽ/ቤት