Addis Zemen (Jun 29, 2026)
ያገለገለ ተሸከርካሪ በጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ችልድረን ክሮስ ኮኔክሽን 1 አገልግሎቱን የጨረሰ መኪና እና አገልገሎታቸውን የጨረሱ ፡እቃቸው ለቅያሪ የሚሆን እና ለመነዳት የማይሆኑ ሞተር ሳይክሎች ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል።
1. የጨረታውን ይክመንት ስለመግዛት፡- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ / ብቻ በመክፈል ወላይታ ሶዶ ከተማ ከድርጅቱ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት የሚሸጠው ወላይታ ሶዶ ባለው በድርጅቱ ቢሮ ቀርበው መመልከት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ለሚገዙት መኪና የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታው ዶክመንት ውስጥ በተዘጋጀው የመጫረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አስገብተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ ችልድረን ክሮስ ኮኔክሽን ወላይታ ሶዶ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ግቢውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት መኪና እና ሞተር ሳይክል የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ / የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ /በችልድረን ክሮስ ኮኔክሽን/ ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/ሲፒኦ/ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ጋር በታሸገ ፖስታ ውስጥ አብሮ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ጨረታው 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4፡30 ሰዓት በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚከፈት ሲሆን አሸናፊው ወዲያው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ታሳቢ በማድረግ ቀሪውን ገንዘብ በ10 ቀናት ውስጥ ከፍለው ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው። በጨረታው አሸንፈው ከፍለው ለማይወስዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል። የጨረታ አሸናፊዎች መኪኖቹን የማጓጓዣ ወጪዎችንና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎችን ይሸፍናሉ።
5. በጨረታው ለሚሸነፉት ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ/ቢድቦንድ/ የጨረታ አሸናፊው ሙሉ ክፍያውን እንደፈጸመ የሚመለስላቸው ይሆናል።
6. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ፡- ወላይታ ሶዶ በድርጅቱ ዋና ግቢ ስልክ፡ 046 551 2816/0911 720 913
ችልድረን ክሮስ ኮኔክሽን