Reporter (Jul 01, 2026)
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር (ኢቅባማ)
የጨረታ ቁጥር ኢቅባማ/ግጨ-01/2018
ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችና የቢሮ ዕቃዎች ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር (ኢ.ቅ.ባ.ማ.) ለሥራ ሲገለገልባቸው የነበሩ ሞተር ሳይክሎችን፣መኪና የመኪና ጎማዎችን፣ እንዲሁም የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችን እና ኤሌክትሮኒክሶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር ቢሮ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።
2.የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 3፡00-6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 -11፡00 ይሆናል።
3. ተጫራቾች መግዛት ለሚፈልጉትን ንብረቶች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚገዙበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር ሥም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ነገር ግን በተጠየቀው መሠረት ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውድድር ውጪ ይደረጋል።
4. ተጫራቾች መግዛት ለሚፈለጉትን ንብረት/ የመግዣ ዋጋ በተያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ብቻ በመሙላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚዘጋበት ቀንና ሰዓት ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት በሰም በታሸገ ኤንቨሎ ∅ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ከታች በተገለጸው አድራሻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (ለአስራ አምስት) የሥራ ቀናት አየር ላይ ይውል እና በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ይህ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የቀን መቁጠሪያ (ካላንደር) የሚዘጋቸው በአላት ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
8. ተጫራቾች የሚከተሉትን ሰነዶች የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
9. ለድርጅቶች የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
10. ለግለሰቦች፦ የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ (ወይም ፓስፖርት/መንጃ ፈቃድ) ኮፒ ማቅረብ ግዴታ ነው።
11. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች /ቾች/ አሸናፊነቱ /ታቸው/ ከተገልጸለት /ላቸው/ በኋላ በ10 (አስር) የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን /ያሸነፉበትን/ ዋጋ በሙሉ መክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርበታል /ይኖርባቸዋል/። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻለ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለኢ.ቅ.ባ. ማ. ገቢ ይደረጋል።
12. ማሕበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በቦሌ መንገድ፣ ከቦሌ ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት ከሚገኘው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቦሌ ቅርንጫፍ ጀርባ፣ ከኢዮብ የድንኳን ሥራዎች እና የድግስ ዕቃዎች ማከራያ አጠገብ፣ በቀድሞው ራስ ከበደ መንገሻ ቤት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር ጽ/ቤት
የቢሮ ስልክ ቁጥር ፡- 011 515 8802 / 09 29 14 73 42
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Phone no:-+251-11 515 8802 Email: Ethiopian.heritage.trust@gmail.com
Bole Road in front of Bole printing House or behind the bole branch commercial bank of Ethiopia Located in the Old house of Ras Kebede Mengesha