በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር የፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት በአስተዳደር ስር ለሚገኙ ለባለበጀት መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ግዢዎችና አገልግሎት ስራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር የፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት በአስተዳደር ስር ለሚገኙ ለባለበጀት መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ግዢዎችና አገልግሎት ስራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Lessan (Jul 11, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 12/13/2019

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር የፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት በአስተዳደር ስር ለሚገኙ ለባለበጀት መስሪያ ቤቶች የተዘረዘሩትን ግዢዎችና አገልግሎት ስራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

  1. ሎት የፅህፈት መስሪያ እና ሌሎች አላቂ የቢሮ እቃዎች
  2. ሎት 2 አላቂ የፅዳት እቃዎች
  3. ሎት 3 የደንብ ልብስና የተለያዩ የስራ ጫማዎች
  4. ሉት 4 የስፖርትና የጅምናዚየም እቃዎች
  5. ሎት 5 የቋሚና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችና ፈርኒቸር
  6. ሎት 6 የህዝብ ትራንስፖርት መኪና፣ የጭነት የመኪና ኪራይ እና የመኪና ሰርቢስ ጥገና
  7. ሎት 7 የህትመት እና ማስታወቂያ ስራዎች፣ ዲጄ ዲኮርና ሳውንድ ሲስተም
  8. ሎት 8 የቢሮ ህንጻ/ ማጠቃለያ ስራ፣ የቢሮ እድሳት እና የፈርኒቸር ጥገና
  9. ሎት 9 የዶሮ ቤት ስራ /ኬጂ/ እና የ90 ቀን ጫጩት
  10. ሎት 10 በወረዳው ለሚከናወኑ የጉልበት ስራዎች

ማሳሰቢያ

1. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የቫት ሰርተፊኬት የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ህጋዊ ማስረጃ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል።

2. ተጫራቾች ከላይ ከተዘረዘሩት ለሁለት ወይም ከዚያ በላይ ለሆኑ እቃዎችና ቁሳቁሶች የሚወዳደሩ ከሆነ ለእያንዳንዱ ዘርፍ ያወጡት ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡትን ሰርተፊኬት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት ሊስት ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እቃዎች ናሙና መስሪያ ቤቱ በሚፈልገው መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት መቅረብ አለበት።

5. ተጫራቾች የጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾች ከሆኑበት የጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁበትን እና ህጋዊ ሰርተፊኬት ከአደራጁ መስሪያ ቤት የተሰጣቸውን ወቅታዊ አምራች መሆናቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ከሌሎች ዶከመንቶች ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በመደበኛ የስራ ሰዓት ከጽ/ቤቱ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመስሪያ ቤቱ ፍላጎት መሰረት ብቻ በመሙላት የተሟላ የመወዳደሪያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በሁለት የተለያየ ፖስታ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል የሚያስገቡት ዋጋ በነጠላ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል።

8. የጨረታ ሳጥኑ በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ይከፈታል።

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና፡- ለሎት 1 ለተቀመጠው 25,000.00 ለሎት 2. 30,000.00 ለሎት 3. 35,000.00 ለሎት 4 20,000.00 ለሎት 5. 40,000.00 /ለሎት 6. 15,000.00 ለሎት 7. 10,000.00 ለሎት 8. 15,000.00 ለሎት 9. 10,000.00 ለሎት 10. 5,000.00 ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

10. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን ማንኛውም ሁኔታ መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይንም ከጨረታ ራሱን ማግለል አይችልም።

11.ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች እስከ መስሪያ ቤቱ የንብረት ክፍል ድረስ በራሳቸው መጓጓዣና የጉልበት ወጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0115574183 በመደወል ወይንም ኦሎምፒያ አካባቢ ከጌቱ ኮሜርሻል ሴንተር በጀርባ በኩል ከሚገኘው የወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት መጠየቅ ይቻላል።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት