Addis Zemen (Jul 20, 2026)
1ኛ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 001/2019
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 1ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 . አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት2. ደንብ ልብስ
- ሎት3. ጽዳት እቃ
- ሎት4. የህትመት ስራዎች
- ሎት5. የፈርኒቸር እቃዎች
- ሎት6. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት7.የኤሌክትሮኒክስ ጥገና የእጅና የማቴሪያል ዋጋ ጨምሮ
- ሎት8.የመስተንግዶ አገልግሎት
- ሎት 9.የቢሮ እቃዎች ጥገና የእጅና የማቴሪያል ዋጋ ጨምሮ
- ሎትıዐ. የመኪና እና የሞተር ሣይክል ጎማ
- ሎት11 የትራንስፖርት አገልግሎት
- ሎት12.የጉልበት ሰራተኛ
- ሎት 13. የድንኳን ኪራይ
- ሎት14.የሰራተኛ ካፌ(ከበብ)
- ሎት15.የስፖርት ትጥቅ
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች
በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ከላይ ከተራ ቁጥር 1-15 ለተጠቀሰው እቃ በዘርፉ ሕጋዊና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
- ቲን ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆኑን በአቅራቢዎች ዝርዝር www.ppa.go.et ላይ የተመዘገበ መሆኑን የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የገዙትን መደበኛ የጨረታ ሰነድ በተጫራች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች በአግባቡ ተሞልቶና በድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ተደርጎበት ሙሉ ሰነዱ መመለስ አለበት፡፡ ሰነዱን ያልመለሰ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከዊንጌት ወደ አጠና ተራ በሚወስደው መንገድ ብስራት የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤትአጠገብ አ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 13 አስተዳደር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 17 ፋይናንስ ጽ/ቤት በመገኘት ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎቶች በ0.5 % ሲሆን ሎት 1. 13,750 (አስራ ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ብር) ሎት2. 21,000(ሃያ አንድ ሺህ ብር) ሎት3. 2,500 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) ሎት4. 5,200 (አምስት ሺህ ሁለት መቶ ብር) ሎት5. 6,000 (ስድስት ሺህ ብር) ሎት6. 6,000 (ስድስት ሺህ ብር) ሎት7. 2,800 (ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ብር) ሎት8. 12,250 (አስራ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) ሎት9. 4,000 (አራት ሺህ ብር) ሎት 10. 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) ሎት 11. 1,000 (አንድ ሺህ ብር) ሎት.12 የጉልበት ሰራተኛ 1000 (አንድ ሺህ ብር) ሎት13. የድንኳን ኪራይ 1000( አንድ ሺህ ብር) ፤ ሎት14.የሰራተኛ ካፌ (መዝናኛ ክበብ) 12,250 (አስራ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) ሎት 15.የስፖርት ትጥቅ 3,000(ሶስት ሺህ ብር) ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ CPO ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች እያንዳንዱን የሚሸጠበትን ነጠላ ዋጋና የጠቅላላውን ዋጋ ከነቫቱ በመግለጽ በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውንና የጨረታውን አይነት በመጥቀስ ከዊንጌት ወደ አጠና ተራ በሚወስደው መንገድ ከብስራት ኛ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ አ/ከ/ከ/ከተማ ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዘርፋቸው የተጠቀሰውን እቃ በሙሉ መጫረት ይችላሉ፡፡
- ሁሉም ተጫራቾች ሰነዱን ሞልተው ሲያስገቡ የእቃውን ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ናሙና ካላቀረቡ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ የመጨረሻው ቀን በ10ኛው ቀን እስከ ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሸጎ በእለቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ጽ/ቤት ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 ውስጥ ይሆናል፡፡
- ቀጣዩ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተራ ቁጥር 1 በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ተፈፃሚ ይደረጋል፡፡
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- በጥቃቅን የተደራጁ አካላት የሚያቀርቡት የዋስትና ደብዳቤ የተደራጁበት ዘርፍ በግልፅ የተቀመጠና አምራች ከሆነ የሚያመርተው ዘርፍ በግልፅ የተቀመጠና ደብዳቤውን ለመፈረም ስልጣን በተሠጠው አካል የተፈረመና የዋስትና ደብዳቤው ለጨረታ ማስከበሪያና ለውል ማለት አለባቸው፡፡
- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም ፡፡
- የጨረታ አሸናፊነቱ ሲረጋገጥ በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውል ለመዋዋል ፈቃደኛ የሆነ እና እቃውንም ለማቅረብ በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ፡፡
- ጨረታ ተወዳድሮ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ውል ለመዋዋል ሲመጡ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% cpo የውል ማስከበርያ አሰርተው መምጣት አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ውል ከወሰደ በኃላ እቃውን በተቋሙ ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡– ቋሚ እቃዎች ተጫራቾች በጽ/ቤቱ ባስቀመጠው እስፔስፊኬሽን መሰረት አስቀድሞ ከሰነዱ ጋር የእቃውን ፎቶ ማስገባት አለባቸው፡፡ ከተቀመጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ የሚቀርብ እቃ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የሁሉንም ሎቶች ስፔስፊኬሽን (ፍላጎት መግለጫ) በጨረታ ሰነዱ በክፍል ስድስት (6) ማየት ይቻላል፡፡
ስልክ ቁጥር፡– 011-273-99-40
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት