Addis Zemen (Aug 17, 2026)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ግ/ጨ/01/2019ዓ.ም
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት የመኪና እስክራፕ እና ሌሎች ቁርጥራጭ ብረታ ብረት፡ መሸጥ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች ላይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ፡–
1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ የዘመኑ ግብር የከፈሉና የተሟላ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. የTIN No ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የንግድ ምዝገባ ቁጥርና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. ግብይቱ ከ 200000 ሺ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተጨማሪ እሴት ተመዝጋቢ መሆን አለባችው፡፡
4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሀሳብ መስጫ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
5. የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
6. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ሆኖ ለወደፊት በመንግስት የሚወጣ ጨረታ እንዳይሳተፉ ሊደረግ ይችላል፡፡
7.ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የክፊያና ሂሳብ ደጋፊ የስራ ሂደት ማግኘት ይችላሉ፡፡
8. የሚገዙትን ማቴሪያሎች ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ከሠነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ዋናውና ኮፒውን ብቻ ለብቻ ከሁሉም የንግድ ማስረጃዎቻቸው ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው::
10. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከ 11/12/2018 አስከ 26/12/2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን 16ኛው ቀን ማለትም 26/12/2018 በ4፡00 ሰዓት የሚታሸግ ይሆናል፡፡
11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻች በተገኙበት በዚሁ ቀን 26/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡30 በጨ/ሮ ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በግልፅ የሚከፈት ሲሆን ምናልባት 16ኛው ቀን የህዝብ በዓል ወይም ከመንግስት የስራ ቀን ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1% በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ጋራንት (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
12. የጨረታ ማስከበሪያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የመጣ የጨረታ ሠነድ ከጨረታ ሳጥን ውስጥ ሳይገባ ተመላሽ ይሆናል።
13. መ/ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፦
- መ/ቤቱ ግዥውን በነጠላ ዋጋ ወይም በሎት ሲያወዳድር ይችላል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912 120 388 / 0919 935 177/ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- አድራሻችን ጨፋ ሮቢት ከተማ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ መስመር 300 ኪ/ሜ ላይ እንገኛለን፡፡
በአብክመ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ/ጽ/ቤት