የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎች (ዴስክቶፕ ኮምፕዩተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ የተለያዩ አይነት ቴሌቨዢኖች፣ የመኪና ጎማ፣ የተለያዩ የውሃ እቃዎች፣ የነዳጅ ታንከር እና ሌሎች እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎች (ዴስክቶፕ ኮምፕዩተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ የተለያዩ አይነት ቴሌቨዢኖች፣ የመኪና ጎማ፣ የተለያዩ የውሃ እቃዎች፣ የነዳጅ ታንከር እና ሌሎች እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 18, 2026)

የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎችን ለመሸጥ 3ተኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ጅግጅጋ/ስተ/003/2018

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በጅግጅጋ ቅርንጫፍ /ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎች (ዴስክቶፕ ኮምፕዩተሮች፣ፕሪንተሮች፣ የተለያዩ አይነት ቴሌቨዢኖች፣ የመኪና ጎማ፣ የተለያዩ የውሃ እቃዎች፣የነዳጅ ታንከር እና ሌሎች እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡

1) ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጅግጅጋ በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጅግጅጋ ቅርንጫፍ /ቤት ቅጥር ግቢ ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ከፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከነሐሴ 11/2018 / ጀምሮ እስከ ነሐሴ 22/2018 . ከቀኑ 6:00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።

2) በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት/Refugees and Returnees Service /በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ የባንክ ዋስትና / Bank Guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3) ማንኛውም ተጫራች ከነሐሴ 11 እስከ ነሐሴ 22/2018 . ድረስ ባሉት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ጅግጅጋ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ጅግጅጋ ቅርንጫፍ /ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት/ መጎብኘት/ ይችላል።

4) ጨረታው ጅግጅጋ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ጅግጅጋ ቅርንጫፍ /ቤት ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ነሐሴ 22/2018 ከቀኑ 830 ታሽጎ በዕለቱ ማለትም ነሐሴ 22/2018 ከቀኑ 900 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5) የጨረታ አሸናፊ ተጫራቶች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋሰትና 3 ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

6) ተጨራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ ይኖርባቸዋል።

7) በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8) ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋቸውን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ እና ለንባብ አስቸጋሪ የሆኑ ፅሑፎች /የዋጋ አሞላል ስህተት/ ከጨረታው ሙሉ በሙሉ ውድቅ ያደርጋል።

9) ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የተቀመጡትን ማሳሰቢያዎችን በአግባቡ መተግበር ይኖርባቸዋል።

10) አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11) ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥር +251 92 936 1915 +251 93 433 5030 +251 91 574 1708 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የጅግጅጋ ቅርንጫፍ /ቤት