የሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በሲዳማ ክልላዊ መንስት በአለታወንዶ ከተማ አስተዳደር የወጣት ሴቶችና ልጃረዶችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያግዝ የሼድ ጥገና በተዘጋጀው ዲዛይን መሠረት ጥቃቅን እና አነስተኛ በብረታ ብረት፤ እንጨት ሥራ እና አሉሚኒየም ስራ ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በሲዳማ ክልላዊ መንስት በአለታወንዶ ከተማ አስተዳደር የወጣት ሴቶችና ልጃረዶችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያግዝ የሼድ ጥገና በተዘጋጀው ዲዛይን መሠረት ጥቃቅን እና አነስተኛ በብረታ ብረት፤ እንጨት ሥራ እና አሉሚኒየም ስራ ማሰራት ይፈልጋል


Reporter (Aug 19, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ
የሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት

የሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በሲዳማ ክልላዊ መንስት በአለታወንዶ ከተማ አስተዳደር የወጣት ሴቶችና ልጃረዶችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያግዝ የሼድ ጥገና በተዘጋጀው ዲዛይን መሠረት ጥቃቅን እና አነስተኛ በብረታ ብረት፤ እንጨት ሥራ እና አሉሚኒየም ስራ (የጋራ ሼርክና ዘርፍ ብቻ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ማህበራት መካከል ጨረታውን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::

በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት መወዳደር ይችላሉ፡-

1.በብረታ ብረት እና እንጨት: አሉሚኒየም ሥራ ዘርፍ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ማህበራት፤

2. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ማህበራት፣

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ማህበራት፣

4. ተጫራቾች ለጨረታ ካስገቡት ጠቅላላ ዋጋ ከተጨ.እሴ.ታክስ ጋር በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) 2% ሲ ፒ ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት::

5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ የሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ቢሮ (ሀዋሳ ፒያሳ በሚኘው ንብ ህንፃ ስምንተኛ ፎቅ) በመቅረብ ይህ ጨረታ በአካባቢ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21,12,2018 (28/08/ 2026) ተከታታይ 10 ቀናትንና ሠዓት በመጠቀም ብር 1000 /አንድ ሽ ብር / በመክፈል መግዛት ይችላሉ፤

6.የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናልና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል፡ አንድ ኦሪጂናልና አንድ ኮፒ ቲክኒካል በአጠቃላይ በአንድ ትልቅ ኤንቬሎፕ ውስጥ በሰም በማሸግ እና በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስክ 21,12,2018 (28/08/ 2026) ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በሥራ ቀንና ሠዓት በሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት (ሀዋሳ ፒያሳ በሚኘው ንብ ህንፃ ስምንተኛ ፎቅ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 9.30 ሠዓት በሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ ቤት (ሀዋሳ ፒያሳ በሚኘው ንብ ህንፃ ስምንተኛ ፎቅ ፎቅ) ይከፈታል:: ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚከፈት ይሆናል:: የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው በተመሣሣይ ሠዓት የሚከፈት ይሆናል::

8.መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ስልክ ቁጥር 0939064059/0911331955

የሄልቬታስአፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሀዋሳ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *