Addis Zemen (Sep 26, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ፤ ግ/ጨ/ቁ 03/2019
በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የኣሪ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ በፑል ለሚተዳደሩ መ/ቤቶች የሠራተኛ ደንብ ልብስ፣ የጽሕፈት መሣሪያ፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፤ የሕትመት አገልግሎት፣ የታሸገ መጠጥ ውሃ፣ ኤሌክትሮኒክስ፤ ሞተር ሣይክል፣ የመኪና ጎማ፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሕንፃ ቁሣቁስ የብሄረሰብ ባሕል አልባሳት፤ የመስተንግዶ አገልግሎት፣ አዳራሽ ዲኮሬሽን፣ ድንኳን ኪራይ አገልግሎት የተማሪ ቀለብ ማጣፈጫ፣ አታክልት እና ማገዶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
በሁሉም መስኮች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ፍቃድ ያሳደሱ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (tin number) እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሠርተፍኬት (VAT) ማስረጃ ያለው፣ የንግድ የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፤ እንዲሁም
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሠራተኛ ደንብ ልብስ 40,000ብር፣ የጽሕፈት መሣሪያ 20,000ብር፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች 10,000 ብር፤ የሕትመት አገልግሎት 5,000ብር ፣ የታሸገ መጠጥ ውሃ 20,000ብር፣ ኤሌክትሮኒክስ 10,000ብር፣ የሞተር ሣይክል 20,000ብር፤ የመኪና ጎማ 20,000ብር፣ የመኪና መለዋወጫ 20,000ብር፣ የሕንፃ ቁሣቁስ 3,000ብር፣ የብሄረሰብ ባሕል አልባሳት 3,000ብር፣ አዳራሽ ዲኮሬሽን 3,000ብር፣ ድንኳን ኪራይ አገልግሎት 5,000ብር፣ የተማሪ ቀለብ 30,000ብር፣ ማጣፈጫ 20,000ብር 1 አታክልት 3,000ብር እና ማገዶ 10,000ብር ማቅረብ አለባቸው፡፡
ከላይ የተገለጹት ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200ብር በመክፈል ከኣሪ ዞን ፋይናንስ ፕ/ል/መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 12 ቀርቦ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
የጨረታውን ሰነድ በ16ኛው /አስራ ስድስተኛው ቀን የሥራ ቀን ከሆነ ካልሆነ በቀጣይ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡30 ሰነዱን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚያው ቀን 8፡30 ሰዓት ባለቤቱ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው ሲከፈት የተጫራቾች ያለመሟላት የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0916-13-59-77
በደቡብ ኢ/ክልል ኣሪ ዞን ፋይናንስ ፕ/ል መምሪያ ጂንካ