Addis Zemen (Sep 28, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ሰነድ ቁጥር PPS/NVP-11FBl/04/01/2019 የኢ. ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአርዳይታ ግብርና ሙያ ትምህርት (ስልጠና ኮሌጅ፣ የፌዴራል የሥነምግባርና የፀረ -ሙስና ኮሚሽን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ቁጥር 1 ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ፤ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፤ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን፣ የግብርና ሚኒስቴር፣ የአጋርፋ የግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርት ሥልጣና ኮሌጅ እና የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የሆኑ 8 ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1. በጨረታው ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ተጫራች ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ማቅረብ ያስፈልጋል።
2. ተጫራቾች 6 ኪሎ በሚገኘው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ ቢሮ በመምጣት የብረቶቹን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመንግሥት ግዥ አገልግሎት የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000003785018 ላይ ገቢ በማድረግና ያስገቡበትን የባንክ ስሊፕ ይዘው በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ብረታ ብረቶቹን ከላይ በተጠቀሱት መ/ቤቶች በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ቁርጥራጭ የብረታ ብረት ዓይነት የጨረታ መነሻ ጠቅላላ ዋጋውን 2% (ሁለት በመቶ) ነገር ግን ብር 100,000 መቶ ሺህ ያልበለጠ ዋስትና ያላስያዘ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው።
5. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።
6. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይሆናል። ይሁንና የብረታ ብረቶቹን ጠቅላላ ግምታዊ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) ነገር ግን ብር 100,000 መቶ ሺህ ያልበለጠ ዋስትና ያላስያዘ እንዲሁም በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
7. የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ላይ ካልሆነ (ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ) ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስቀረውም።
8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖር ባቸዋል። ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ብረታ ብረቶችሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አተገባበርዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አሰር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
10. ተጫራቾች ያሸነፉትን ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ የሚዛንና ሌሎች ወጪዎችን በመሸፈን ብረታ ብረቱ ከሚገኝበት ስፍራ ቅርብ በሆነ ፕሪንት አውት ማውጣት በሚችል የመንግስት የምድር ሚዛን በማስመዘን ውል በፈረሙ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቱን በማንሳት ማጠናቀቅ አለባቸው። ግምታዊ መጠኑ ከፕሪንት አውት ከሚገኘው ትክክለኛ የብረቱ መጠን ጋር የሚኖረው ልዩነት ታስቦ አሸናፊው ተጫራች ተጨማሪ ክፍያ የሚኖርበት ከሆነ የውል ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ልዩነት የሚኖረውን ሂሳብ መክፈል ያለበት ሲሆን በትርፍነት የሰጠው ተመላሽ የሚደረግለት ገንዘብ ካለም በአገልግሎቱ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል።
11. አገልግሎቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።
12. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
13. አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ወይም ሌላ ጨረታውን ለመሰረዝ የሚያበቃ ምክንያት ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው
አድራሻ፡- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት 6 ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት አደባባይ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ፡ www.pps.gov.et ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል።
የፌዴራል መንግስት ግዥ አገልግሎት