በኢፌዲሪ ኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የኮንስትራክሸን ማሸነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ ብረታ ብረት፣ የምርት ግብአት እና የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት እና የአደጋ መከላከያ ዕቃዎች ግዥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኢፌዲሪ ኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የኮንስትራክሸን ማሸነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ ብረታ ብረት፣ የምርት ግብአት እና የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት እና የአደጋ መከላከያ ዕቃዎች ግዥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 19, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ቁጥር ኮማማኢ/ሰቼማ/001/2018

በኢፌዲሪ ኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የኮንስትራክሸን ማሸነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የግዥ አይነት፦

  • በሎት 1 ጥሬ ዕቃ ብረታ ብረት
  • በሎት 2 የምርት ግብአት
  • በሎት 3 የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት እና የአደጋ መከላከያ ዕቃዎች

የተጫራቾች መመሪያና ግዴታ

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ
  2. የግብር ከፉይነት የተመዘገቡና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TIN NO ያላቸዉ
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  4. ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ሎት ጠቅላላ ዋጋ VAT ጨምሮ ብር 2% በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ሲፒዩ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸዉ።
  5. ተጫራቾች ዋጋ ሞልተዉ የሚያቀርቡት ከዚህ ሰነድ ጋር ተያይዞ በቀረበዉ የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ብቻ ይሆናል በዋጋ መሙያ ቅፅ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ እጅግ የተከለከለ ነዉ።
  6. ማንኛዉም ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
  7. የመወዳደሪያ ሰነዱን የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር ከ00/100) በመክፈል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከላንድ ማርክ ሆስፒታል ትይዩ በሚገኘዉ ጠማማ ፎቅ ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 15 አንደኛ ፎቅ ላይ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በቀረበዉ ዝርዝር በመሙላት የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ዉስጥ ኢንዱስትሪዉ ባዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ።
  9. የጨረታ ማስገቢያ ቀንና ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚቀርብ ጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም።
  10. የጨረታ መክፈቻ ቀን በሕዝብ በዓላት ቀን ከዋለ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ በዓሉ በዋለ በማግስቱ ይሆናል።
  11. ጨረታዉ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት በጨረታ ሰነድ ላይ የሚጠቀስ ይሆናል።
  12. የጨረታ አሸናፊ የሆነዉ ድርጅት አሸናፊ መሆኑን በደብዳቤ ከተገለፀበት በኃላ በሦስት ቀን ዉስጥ ቀርቦ ዉል በመዋዋል ንብረቱን በኢንዱስትሪዉ ቅጥር ግቢ ማቅረብ አለበት።
  13. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸዉን ኦርጅናሉንና ኮፒውን ለየብቻ በፖስታ አሸገዉ ማቅረብ አለባቸዉ።
  14. ኢንዱስትሪዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
  15. አድራሻ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከላንድ ማርከ ሆስፒታል ትይዩ በሚገኘዉ ጠማማ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 15 አንደኛ ፎቅ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 23 80 19 15/ 09 81 70 27 70 ደዉለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።

ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ

የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *