በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለላስታ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለላስታ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 05, 2026)

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨ/ መለያ ቁጥር ግ/ን/አ/ስ/፡-18/2019

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለላስታ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡–

  • ሎት 01 ቆርቆሮ ሚስማር ብረታ ብርትና ሌሎች የግንባታ እቃዎች፣
  • ሎት 02 የሲሚንቶ አቅርቦት፣
  • ሎት የመኪና ጎማ፣
  • ሎት 4 ጣውላ፣
  • ሎት 05 የጽህፍት መሳሪያ፣
  • ሎት 06 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • ሎት 07 የጽዳት እቃዎች፣
  • ሎት 08 የስፖርት ትጥቅ፣
  • ሎት 09 HDEP ፕላስቲክ እቃዎች ግዥ በመደበኛና በተራድኦ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

1. በአዲሱ የንግድ አዋጅ መሠረት የእያንዳንዱ ሎት የተናጠል በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነበር/ ሰርተፍኬት ያላቸውና፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚገልጽ የግብር ክሊራንስ ፣ የንግድ ምዝግባ የምስክር ወርቀት እና የሚሞሉት ዋጋ ከ500000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ሰርተፍኬት ማቅርብ አለባቸው።

2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.3 በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢት ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ለሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ለጨረታ ማስከበሪያ በተጫራቾች መመሪያ በተቁ

8 ላይ የተገለጸውን የገንዘብ መጠን ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዥያ (CPO)፤ በሆኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (BID BOND): በባንክ በተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከፖስታው ውስጥ አብሮ መግባት ይኖርበታል።

4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ የሚቆጠር ለ10 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ11ኛው ቀን፡– ሎት 01 ቆርቆሮ ሚስማር ብረታ ብርትና ሌሎች የግንባታ እቃዎች፣ሎት ዐ2 የሲሚንቶ አቅርቦት እቃዎች ፤ ሎት4 ጣውላ፤ ሎት 09 HDEP ፕላስቲክ እቃዎች ጠዋት 3፡45 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እንዲሁም በዚሁ ቀን፡– ሎት 05 የጽህፍት መሳሪያ፤ ሎት 06 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ሎት 07 የጽዳት እቃዎች ሎት 08 የስፖርት ትጥቅ፤ ሎት 3 የመኪና ጎማ ከሰዓት 8፡15 ታሽጎ 8፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5. የተጠቀሰው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ ለሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይተላለፋና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል።

6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን ኮፒና ኦርጂናል በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

7. አሸናፊው አካል እቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት ላስታ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች መጋዘን ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል።

8. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

9. ተጫራቾች በአንድ ሎት ውስጥ የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም ውድድሩ በየሎት ምድብ ጥቅል ድምር ስለሆነ የሁሉም እቃ ዋጋዎች መሞላት አለበት።

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

11. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመቅረብ ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሱት

ስልክ ቁጥሮች፦ 03333601249፤ ወይም 0984148814 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት