Addis Zemen (Nov 19, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በ18/03/2019 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ በኦክሽን ኢትዮጵያ(auction ethiopia) መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታውመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች መተግበሪያውን ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር auction Ethiopia ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ በመመዝገብና የጨረታ ሰነዱን በማየት፣ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፣ የእቃዎችን ሳምፕልም ከኦክሽን ኢትዮጵያ ድህረ–ገጽ (auction ethiopia page) ወይም አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
የጨረታ መስፈርቶች፡ –
1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ሰለ መሆኑ ክልራንሰ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክለ እንቅሰቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምሰክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በሲስተም አታች ማድረግ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን በ18/03/2019 ዓ/ም ከኦክሽን ኢትዮጵያ ድህረ–ገጽ(action Ethiopia page) ማየት ይችላሉ።
3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በማስያዝ በሲስተም አታች ማድረግ ይኖርባቸዋል
|
ተ.ቁ |
አጫራች ቅ/ጽ/ቤት |
የጨረታው ዓይነት |
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች |
የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
አዋሽ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት |
ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ |
ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞባይል ቀፎና አሰሰሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ፣ የስፖርት እቃዎች፣የእጅ ሰዓት ኮስሞቲክስ ፣ መነዕር፣ጌጣ ጌጥ፣ የሳሙና ፋብሪካ አካል ማሽነሪ፣ ተሸከርካሪ እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች |
ለግልጽና ለሐራጅ ጨረታ በ18/03/2019 እስከ ከሰዓት 9፡45 |
ለግልጽ ጨረታ መዝጊያ ጊዜ በ18/03/2019 ዓ/ም ከሰዓት 10፡00 ፣ ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ 18/03/2019 ዓ/ም 11:00 ሰዓት ይሆናል። |
4. የጨረታው መክፈቻ ሰዓት እና ቀንን ከኦክሽን ኢትዮጵያ ድህረ–ገጽ(auction Ethiopia page) በማየት የጨረታው ሂደት ተጀምሮ ከማለቁ በፊት ዋጋ መስጠት ይችላሉ።
5. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋሰትና ያስያዙት (c.p.o) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፈ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
6. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውሰጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖረበታል።
7. ከላይ በተቁ7 በተገለጹት ቀናት ውሰጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረከበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማሰከበሪያ ያያዙት ገንዘብ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሸኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል።
8. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. የኦክሽን ኢትዮጵያ(auction ethiopia) መተግበሪያን በተመለከተ የጥሪ ማእከሉን ሠራተኛ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 09-05-11-55-11 / 011-666 8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-13-97-49-27 ይደውሉ።
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት